1
ወደ ሮም ሰዎች 5:8
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል።
Vertaa
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:8
2
ወደ ሮም ሰዎች 5:5
በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ሞላ ተስፋው አያሳፍርም።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:5
3
ወደ ሮም ሰዎች 5:3-4
በዚህ ብቻ ሳይሆን መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝልን ስለምናውቅ በመከራችንም እንመካለን። ከትዕግሥትም በፈተና መጽናት፥ ከመጽናትም ተስፋ ይገኛል።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:3-4
4
ወደ ሮም ሰዎች 5:1-2
እንግዲህ እኛ ጽድቅን ያገኘነው በእምነት ስለ ሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን። ወደዚህ አሁን በእምነት ጸንተን ወደምንገኝበት ጸጋ የገባነው በእርሱ ስለ ሆነ በተስፋ የእግዚአብሔር ክብር ተካፋዮች በመሆናችን እንመካለን።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:1-2
5
ወደ ሮም ሰዎች 5:6
ገና ደካሞች ሆነን ሳለ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:6
6
ወደ ሮም ሰዎች 5:9
እንግዲህ የጸደቅነው በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከሆነ ይበልጡንም ከእግዚአብሔር ቊጣ የምንድነው በእርሱ አማካይነት ነው።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:9
7
ወደ ሮም ሰዎች 5:19
በአዳም አለመታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ እንዲሁም በክርስቶስ መታዘዝ ምክንያት ብዙዎች ይጸድቃሉ።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:19
8
ወደ ሮም ሰዎች 5:11
ይህም ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነትም በእግዚአብሔር እንመካለን።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 5:11
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot