1
ወደ ሮም ሰዎች 10:9
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በአፍህ ብትመሰክርና እግዚአብሔር ከሞት እንዳስነሣውም በልብህ ብታምን ትድናለህ።
Vertaa
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:9
2
ወደ ሮም ሰዎች 10:10
ሰው በልቡ ሲያምን ይጸድቃል፤ በአፉም ሲመሰክር ይድናል፤
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:10
3
ወደ ሮም ሰዎች 10:17
ስለዚህ እምነት የሚገኘው የምሥራቹን ቃል ከመስማት ነው፤ የምሥራቹም ቃል የሚገኘው ስለ ክርስቶስ ከሚነገረው ትምህርት ነው።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:17
4
ወደ ሮም ሰዎች 10:11-13
በቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፦ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።” እንግዲህ አንዱ ጌታ የሁሉም ጌታ ስለ ሆነ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ምንም ልዩነት የለም፤ እርሱም ለሚለምኑት ሁሉ በረከቱን አብዝቶ ይሰጣል፤ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” ተብሎአልና።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:11-13
5
ወደ ሮም ሰዎች 10:15
አስተማሪዎች ካልተላኩስ እንዴት ቃሉን ሊያስተምሩ ይችላሉ? ይህም “የመልካም ዜና አብሣሪዎች መምጣት እንዴት ደስ ያሰኛል!” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:15
6
ወደ ሮም ሰዎች 10:14
ነገር ግን ሳያምኑበት እንዴት ሊጠሩት ይችላሉ? ስለ እርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምናሉ? ያለ አስተማሪስ እንዴት ሊሰሙ ይችላሉ?
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:14
7
ወደ ሮም ሰዎች 10:4
ሰው ሁሉ በእምነት እንዲጸድቅ ሕግ በክርስቶስ አክትሞአል።
Tutki ወደ ሮም ሰዎች 10:4
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot