1
የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ከክፋት ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። እስከ መጨረሻ በትዕግሥት የሚጸና ግን ይድናል።
Vertaa
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:12-13
2
የማቴዎስ ወንጌል 24:14
ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል በመላው ዓለም ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:14
3
የማቴዎስ ወንጌል 24:6
የጦርነትን ድምፅና የጦርነትን ወሬ ትሰማላችሁ፤ ይህ ሁሉ መሆን ስላለበት አትደንግጡ፤ መጨረሻው ግን ገና ነው።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:6
4
የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥትም በመንግሥት ላይ በጦርነት ይነሣል፤ በልዩ ልዩ ስፍራ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል። ይህም ሁሉ እንደ ምጥ ጣር ያለ የጭንቅ መጀመሪያ ይሆናል።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:7-8
5
የማቴዎስ ወንጌል 24:35
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:35
6
የማቴዎስ ወንጌል 24:5
ብዙዎች ‘እኔ መሲሕ ነኝ!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙ ሰዎችንም ያሳስታሉ።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:5
7
የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
በዚያን ጊዜ ሰዎች ለመከራ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ ይገድሉአችኋል፤ ስለ ስሜም በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። በዚያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን በመካድ ይሰናከላሉ፤ አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ሰዎችም እርስ በርሳቸው ይጣላሉ። ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:9-11
8
የማቴዎስ ወንጌል 24:4
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “ማንም ሰው እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ!
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:4
9
የማቴዎስ ወንጌል 24:44
እንዲሁም የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ስለሚመጣ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ።”
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:44
10
የማቴዎስ ወንጌል 24:42
እንግዲህ ጌታችሁ በየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተግታችሁ ጠብቁ።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:42
11
የማቴዎስ ወንጌል 24:36
“ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአብ በቀር የሰማይ መላእክት ቢሆኑ፥ ወልድም ቢሆን፥ ማንም የሚያውቅ የለም።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:36
12
የማቴዎስ ወንጌል 24:24
ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የእግዚአብሔርን ምርጦች እንኳ ለማሳሳት ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
በኖኅ ዘመን እንደ ነበረው ዐይነት፥ የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜም እንዲሁ ይሆናል። በዚያን ዘመን፥ ከጥፋት ውሃ በፊት ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያጋቡና ሲያጋቡ ነበር። የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉንም ጠራርጎ እስከ ወሰዳቸው ድረስ አላወቁም ነበር፤ የሰው ልጅ አመጣጥም ልክ እንዲሁ ይሆናል።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 24:37-39
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot