1
የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፥ በሙሉ ነፍስህ፥ በሙሉ ሐሳብህ ውደድ፤ ከሁሉ የሚበልጠውና የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው። ይህንንም የሚመስለው ሁለተኛው ትእዛዝ፥ ‘ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤’ የሚለው ነው።
Vertaa
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 22:37-39
2
የማቴዎስ ወንጌል 22:40
የሕግና የነቢያት ትምህርት ሁሉ የተመሠረቱት በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዞች ላይ ነው።”
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 22:40
3
የማቴዎስ ወንጌል 22:14
ቀጥሎም ኢየሱስ “ስለዚህ የተጠሩ ብዙዎች ናቸው፤ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው” አለ።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 22:14
4
የማቴዎስ ወንጌል 22:30
በሙታን ትንሣኤ ጊዜ ሰዎች በሰማይ እንዳሉት መላእክት ይሆናሉ እንጂ አያገቡም፤ አይጋቡም።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 22:30
5
የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
ለግብር የሚከፈለውን ገንዘብ እስቲ አሳዩኝ!” አላቸው። ስለዚህ እነርሱ አንድ ዲናር አምጥተው አሳዩት። እርሱም፥ “በዚህ ገንዘብ ላይ የተቀረጸው መልክና የተጻፈው ስም የማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው፤ እነርሱም፥ “የሮማው ንጉሠ ነገሥት ነው!” አሉት፤ እርሱም፥ “እንግዲያውስ የንጉሡን ለንጉሡ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ፤” አላቸው።
Tutki የማቴዎስ ወንጌል 22:19-21
Koti
Raamattu
Suunnitelmat
Videot