Logo de YouVersion
Icono de búsqueda

ትን​ቢተ ዮናስ 3

3
ዮናስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​ዘዙ
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ሁለ​ተኛ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“ተነ​ሥ​ተህ ወደ​ዚ​ያች ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህ​ንም የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ስብ​ከት ስበ​ክ​ላት” አለው። 3ዮና​ስም ተነ​ሥቶ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነ​ዌም ታላቅ ከተማ ነበ​ረች፤ የቅ​ጥ​ር​ዋም ዙሪያ በእ​ግር የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ነበረ። 4ዮና​ስም የአ​ንድ ቀን መን​ገድ ያህል ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦ​ስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች አለ።”#ዕብ. “እስከ አርባ ቀን ድረስ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች” አለ።
5የነ​ነዌ ሰዎ​ችም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመኑ፤ ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታ​ላ​ቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ። 6ወሬ​ውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እር​ሱም ከዙ​ፋኑ ተነ​ሥቶ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አወ​ለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአ​መ​ድም ላይ ተቀ​መጠ። 7ዐዋ​ጅም አስ​ነ​ገረ፤ በነ​ነ​ዌም ውስጥ የን​ጉ​ሡ​ንና የመ​ኳ​ን​ን​ቱን ትእ​ዛዝ አሳ​ወጀ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶች፥ ላሞ​ችና በጎች አን​ዳች አይ​ቅ​መሱ፤ አይ​ሰ​ማ​ሩም፤ ውኃ​ንም አይ​ጠጡ፤ 8ሰዎ​ችና እን​ስ​ሶ​ችም ማቅ ይል​በሱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ን​ድ​ነት ይጩኹ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በእ​ጃ​ቸው ከአ​ለው ግፍ ይመ​ለሱ። 9እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ይምራን፥ ከጽኑ ቁጣውም ይመለስ እንደሆነ ማን ያውቃል?” 10እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።

Destacar

Compartir

Copiar

None

¿Quieres tener guardados todos tus destacados en todos tus dispositivos? Regístrate o inicia sesión