1
ኦሪት ዘጸአት 7:1
መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)
አማ54
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “እይ፤ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል።
Comparar
Explorar ኦሪት ዘጸአት 7:1
2
ኦሪት ዘጸአት 7:3-4
እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ። ፈርዖንም አይሰማችሁም፤ እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ፤ ሠራዊቴንም የእስራኤልን ልጆች ሕዝቤን በታላቅ ፍርድ ከግብፅ አገር አወጣለሁ።
Explorar ኦሪት ዘጸአት 7:3-4
3
ኦሪት ዘጸአት 7:5
ግብፃውያንም፥ እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው ባወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆነሁ ያውቃሉ።”
Explorar ኦሪት ዘጸአት 7:5
4
ኦሪት ዘጸአት 7:11-12
ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቍዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።
Explorar ኦሪት ዘጸአት 7:11-12
5
ኦሪት ዘጸአት 7:17
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል።
Explorar ኦሪት ዘጸአት 7:17
6
ኦሪት ዘጸአት 7:9-10
“ፈርዖን፦ ‘ተአምራትን አሳዩኝ፤’ ሲላችሁ፥ አሮንን፦ ‘በትርህን ወስደህ እባብ እንድትሆን በፈርዖን ፊት ጣላት’ በለው”። ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በባሮቹ ፊት ጣለ፤ እባብም ሆነች።
Explorar ኦሪት ዘጸአት 7:9-10
Inicio
Biblia
Planes
Vídeos