1
ኦሪት ዘፀአት 7:1
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል።
Comparar
Explorar ኦሪት ዘፀአት 7:1
2
ኦሪት ዘፀአት 7:3-4
እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ። ፈርዖንም አይሰማችሁም፤ እጄንም በግብፅ ላይ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ሕዝቤን በኀይሌ በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ሀገር አወጣለሁ።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 7:3-4
3
ኦሪት ዘፀአት 7:5
ግብፃውያንም እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው በአወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
Explorar ኦሪት ዘፀአት 7:5
4
ኦሪት ዘፀአት 7:11-12
ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። እያንዳንዳቸውም በትራቸውን ጣሉ፤ እባቦችም ሆኑ፤ የአሮን በትር ግን በትራቸውን ዋጠች።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 7:11-12
5
ኦሪት ዘፀአት 7:17
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወንዙን ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፤ ውኃውም ወደ ደም ይለወጣል።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 7:17
6
ኦሪት ዘፀአት 7:9-10
“ፈርዖን፦ ተአምራትንና ድንቅን አሳዩኝ ሲላችሁ፥ ወንድምህ አሮንን፦ ‘በትርህን ወስደህ በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባብም ትሆናለች።” ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ጣለ፤ እባብም ሆነች።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 7:9-10
Inicio
Biblia
Planes
Vídeos