1
ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
አማ2000
“ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ።
Comparar
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:2-3
2
ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
“በላይ በሰማይ ከአለው፥ በታችም በምድር ከአለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ከአለው ነገር የማናቸውንም ምስል ለአንተ አምላክ አታድርግ። አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:4-5
3
ኦሪት ዘፀአት 20:12
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:12
4
ኦሪት ዘፀአት 20:8
“የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አስብ።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:8
5
ኦሪት ዘፀአት 20:7
“የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:7
6
ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
ስድስት ቀን ሥራህን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፤ ሰባተኛዋ ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ አህያህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርስዋ ምንም ሥራ አትሥሩ፤
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:9-10
7
ኦሪት ዘፀአት 20:17
“የባልንጀራህን ሚስት፥ የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ እርሻውንም፥ ሎሌውንም፥ ገረዱንም፥ በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከብቱንም ሁሉ ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማንኛውንም አትመኝ።”
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:17
8
ኦሪት ዘፀአት 20:16
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:16
9
ኦሪት ዘፀአት 20:14
“አታመንዝር።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:14
10
ኦሪት ዘፀአት 20:13
“አትግደል።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:13
11
ኦሪት ዘፀአት 20:15
“አትስረቅ።
Explorar ኦሪት ዘፀአት 20:15
Inicio
Biblia
Planes
Vídeos