1
የማቴዎስ ወንጌል 6:33
አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም
አማ05
እናንተ ግን፥ አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ የቀረው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፤
Comparar
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:33
2
የማቴዎስ ወንጌል 6:34
ነገ ለራሱ ይጨነቃል፤ ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።”
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:34
3
የማቴዎስ ወንጌል 6:25
ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ በማለት ስለ ኑሮአችሁ አትጨነቁ፤ ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት አይበልጥምን?
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:25
4
የማቴዎስ ወንጌል 6:6
አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ ክፍልህ ገብተህ፥ በርህን ዝጋና በስውር ወዳለው ወደማይታይ አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:6
5
የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
ስለዚህ እናንተ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፦ ‘በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ! ስምህ ይመስገን፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም በምድር ይሁን።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:9-10
6
የማቴዎስ ወንጌል 6:11
የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:11
7
የማቴዎስ ወንጌል 6:12
እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ በደላችንን ይቅር በለን፤
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:12
8
የማቴዎስ ወንጌል 6:13
ከክፉ አድነን እንጂ፥ ወደ ፈተና አታግባን፤ [መንግሥት፥ ኀይልና ክብር ለዘለዓለም ያንተ ነው፤ አሜን።’]
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:13
9
የማቴዎስ ወንጌል 6:14
“የሰዎችን በደል ይቅር ብትሉላቸው፥ እናንተንም የሰማዩ አባታችሁ ይቅር ይልላችኋል።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:14
10
የማቴዎስ ወንጌል 6:26
እስቲ በሰማይ ላይ ወደሚበሩት ወፎች ተመልከቱ፤ እነርሱ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራ አይከቱም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:26
11
የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት፥ በዚህ ምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ። ይልቅስ ብልና ዝገት ሊያጠፉት በማይችሉበት፥ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብታችሁን አከማቹ። ሀብትህ ባለበት ልብህም በዚያ ይገኛል።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:19-21
12
የማቴዎስ ወንጌል 6:24
“አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች አገልጋይ ሊሆን አይችልም፤ ወይም አንዱን ይጠላል፥ ሌላውንም ይወዳል፤ ወይም አንዱን ያከብራል፥ ሌላውን ይንቃል፤ እንዲሁም አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ አገልጋይ መሆን አይችልም።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:24
13
የማቴዎስ ወንጌል 6:30
ታዲያ ዛሬ ታይቶ ነገ በእሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር፥ እግዚአብሔር እንዲህ የሚያለብስ ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት አብልጦ አያለብሳችሁም!
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:30
14
የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
አንተ ግን ምጽዋት ስትመጸውት ቀኝ እጅህ የሚያደርገውን ግራ እጅህ አይወቅ። እንግዲህ ምጽዋትህ በስውር ይሁን፤ በስውር የተሠራውን የሚያየው አባትህ፥ የመልካም ሥራህን ዋጋ ይከፍልሃል።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:3-4
15
የማቴዎስ ወንጌል 6:1
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሰዎች ይዩልን ብላችሁ መልካም ሥራችሁን በሰዎች ፊት ከማድረግ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ግን፥ በሰማይ አባታችሁ ዘንድ ምንም ዋጋ አታገኙም።
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:1
16
የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አንተ ግን በምትጾምበት ጊዜ ፊትህን ታጠብ፤ ራስህንም ተቀባ፤ በዚህ አኳኋን፥ መጾምህን በስውር ካለው አባትህ በቀር ሌላ ማንም አያውቅም። በስውር የተሠራውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።”
Explorar የማቴዎስ ወንጌል 6:16-18
Inicio
Biblia
Planes
Vídeos