YouVersion Logo
Search Icon

የማቴዎስ ወንጌል 1

1
የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ
(ሉቃ. 3፥23-38)
1የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ መጽሐፍ።
2አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤ 3ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮም አራምን ወለደ፤ 4አራም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤ 5ሰልሞን ከራኬብ#1፥5 ራዓብ። ቦኤዝን ወለደ፤ ቦኤዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤ 6#2ነገ. 24፥14፤15፤ 2ዜ.መ. 36፥10፤ ኤር. 27፥20።እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፤ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ።
7ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ ሮብዓም አቢያን ወለደ፤ አቢያም አሣፍን ወለደ፤ 8አሣፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥ ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራም ዖዝያንን ወለደ፤ 9ዖዝያን ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታም አካዝን ወለደ፤ አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤ 10ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞፅን ወለደ፤ አሞፅም ኢዮስያስን ወለደ፤ 11ኢዮስያስ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ።
12ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤ 13ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤ አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዞርን ወለደ፤ 14አዞር ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤ አኪም ኤልዩድን ወለደ፤ 15ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ 16ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ።
17እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ዐሥራ አራት ትውልድ ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
(ሉቃ. 2፥1-7)
18 # ሉቃ. 1፥27። የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንዲህ ነበር፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳለች ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። 19እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ስለ ነበረ ሊያጋልጣት አልፈለገም፥ በስውርም ሊተዋት አሰበ። 20እርሱ ይህን ሲያስብ ሳለ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለው “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ። 21#ሲራ. 46፥1፤ ሉቃ. 1፥31።ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።” 22ይህ ሁሉ የሆነው ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው እንዲፈጸም ነው፦
23 # ኢሳ. 7፥14። “እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤
ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤”
ትርጉሙም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” ማለት ነው። 24ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቅቶ የጌታ መልአክ እንዳዘዘው አደረገ፤ እጮኛውንም ወሰደ፤ 25#ሉቃ. 2፥21።የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው።

Highlight

Share

Copy

None

Want to have your highlights saved across all your devices? Sign up or sign in