1
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-24
መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)
መቅካእኤ
ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋልና፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲሁ በጸጋው ይጸድቃሉ።
Vergleichen
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:23-24
2
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22
ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለን እምነት የሚገኝ ነው፤ ልዩነት የለምና፤
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:22
3
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤ ራሱም ጻድቅ እንዲሆን በኢየሱስም የሚያምነውን እንዲያጸድቅ አሁን በዚህ ዘመን ጽድቁን እንዲያሳይ ነው።
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:25-26
4
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20
ምክንያቱም በሕግ ሥራ ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት አይጸድቅም፤ በሕግ አማካኝነት ኃጢአት ይታወቃልና።
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:20
5
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-12
እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “ጻድቅ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም፤ የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤ ሁሉም ከመንገድ ወጥተዋል፤ በአንድነትም የማይጠቅሙ ሆነዋል፤ መልካም የሚሠራ አንድም የለም፤ አንድ ስንኳ የለም።”
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:10-12
6
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:28
ሰው ሕግ ከሚያዘው ሥራ ውጭ በእምነት እንደሚጸድቅ እናምናለንና።
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:28
7
ወደ ሮሜ ሰዎች 3:4
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።
Studiere ወደ ሮሜ ሰዎች 3:4
Hauptbildschirm
Bibel
Lesepläne
Videos