Romans 15:5-33

ሮሜ 15:5-33 - ብርታትንና መጽናናትን የሚሰጥ አምላክ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ስትከተሉ፣ በመካከላችሁ አንድ ሐሳብ ይስጣችሁ፤ ይኸውም በአንድ ልብና በአንድ አፍ ሆናችሁ፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት ታከብሩ ዘንድ ነው።
እንግዲህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሆን ዘንድ ክርስቶስ እንደ ተቀበላችሁ፣ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ። ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደ ሆነ እነግራችኋለሁና፤ እንዲሁም አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ ያመሰግኑት ዘንድ ነው፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤
“ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤
ለስምህም እዘምራለሁ።”
ደግሞም፣
“አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ” ይላል።
እንደ ገናም፣
“አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑት፤
ሕዝቦችም ሁሉ ወድሱት” ይላል።
ኢሳይያስም እንዲሁ፣
“በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣
የእሴይ ሥር ይመጣል፤
በርሱም ሕዝቦች ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል።
በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው።

ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተ ራሳችሁ በበጎነት የተሞላችሁ፣ በዕውቀትም ሁሉ የተሞላችሁና አንዱ ሌላውን ለመምከር ችሎታ ያላችሁ መሆናችሁን እኔ ራሴ ርግጠኛ ሆኛለሁ። እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መሠረት፣ እንደ ገና አሳስባችሁ ዘንድ በአንዳንድ ጕዳዮች ላይ በድፍረት የጻፍሁላችሁ፣ በእግዚአብሔር ወንጌል የክህነት ተግባር፣ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ለመሆን ነው፤ ይኸውም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔርን በማገልገሌ በክርስቶስ ኢየሱስ እመካለሁ። በተናገርሁትና ባደረግሁት ነገር አሕዛብ ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ፣ ክርስቶስ በእኔ ሆኖ ከፈጸመው በቀር ሌላ ነገር ለመናገር አልደፍርም፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል፣ በምልክቶችና በታምራት ነበር። በዚህም ሁኔታ ከኢየሩሳሌም እስከ እልዋሪቆን ዙሪያ ድረስ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ። ሌላው በጣለው መሠረት ላይ እንዳልገነባ ብዬ፣ ክርስቶስ ባልተጠራበት ስፍራ ወንጌልን መስበክ የዘወትር ምኞቴ ነበር። ይልቁንም፣
“ስለ እርሱ ያልተነገራቸው ያያሉ፤
ያልሰሙትም ያስተውላሉ”
ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህም ምክንያት ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ ተከለከልሁ።

አሁን ግን በእነዚህ አካባቢዎች የምሠራው ስለሌለ፣ ከብዙ ዓመታት ጀምሮ እናንተን ለማየት እናፍቅም ስለ ነበር፣ ይህን ዕቅድ ወደ እስጳንያ በምሄድበት ጊዜ ልፈጽመው ዐስባለሁ። በማልፍበትም ጊዜ ልጐበኛችሁና ከእናንተ ጋራ ለጥቂት ጊዜ ቈይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ በጕዞዬ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ግን በዚያ የሚገኙትን ቅዱሳን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ላይ ነኝ። ምክንያቱም መቄዶንያና አካይያ፣ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል የሚገኙትን ድኾች ለመርዳት ተነሣሥተዋልና። ርዳታ ለማድረግ ወድደዋል፤ በርግጥም ባለዕዳዎቻቸው ናቸው። አሕዛብ የአይሁድ መንፈሳዊ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ፣ ያገኙትን ምድራዊ በረከት ከአይሁድ ጋራ ይካፈሉ ዘንድ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናቸው። ስለዚህ ሥራውን ከጨረስሁና ይህን ፍሬ መቀበላቸውን ካረጋገጥሁ በኋላ ወደ እስጳንያ እሄዳለሁ፤ እግረ መንገዴንም እናንተን አያለሁ። ወደ እናንተም ስመጣ፣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንደምመጣ ዐውቃለሁ።
ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የተጋድሎዬ አጋር እንድትሆኑ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ። በይሁዳ ካሉት ከማያምኑት እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለው አገልግሎቴም በዚያ ባሉት ቅዱሳን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩልኝ፤ ይኸውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተም ጋራ እንድታደስ ነው። የሰላም አምላክ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን። አሜን።

ብርታትንና መጽናናትን የሚሰጥ አምላክ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ስትከተሉ፣ በመካከላችሁ አንድ ሐሳብ ይስጣችሁ፤ ይኸውም በአንድ ልብና በአንድ አፍ ሆናችሁ፣ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት ታከብሩ ዘንድ ነው። እንግዲህ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሆን ዘንድ ክርስቶስ እንደ ተቀበላችሁ፣ እርስ በርሳችሁ ተቀባበሉ። ለአባቶች የተሰጠውን የተስፋ ቃል ያጸና ዘንድ ለእግዚአብሔር እውነት ሲል ክርስቶስ የአይሁድ አገልጋይ እንደ ሆነ እነግራችኋለሁና፤ እንዲሁም አሕዛብ እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱ ያመሰግኑት ዘንድ ነው፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ስለዚህ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ።” ደግሞም፣ “አሕዛብ ሆይ፤ ከሕዝቡ ጋራ ደስ ይበላችሁ” ይላል። እንደ ገናም፣ “አሕዛብም ሁላችሁ ጌታን አመስግኑት፤ ሕዝቦችም ሁሉ ወድሱት” ይላል። ኢሳይያስም እንዲሁ፣ “በሕዝቦች ሁሉ ላይ የሚነግሠው፣ የእሴይ ሥር ይመጣል፤ በርሱም ሕዝቦች ተስፋ ያደርጋሉ” ይላል። በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው። ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተ ራሳችሁ በበጎነት የተሞላችሁ፣ በዕውቀትም ሁሉ የተሞላችሁና አንዱ ሌላውን ለመምከር ችሎታ ያላችሁ መሆናችሁን እኔ ራሴ ርግጠኛ ሆኛለሁ። እግዚአብሔር በሰጠኝ ጸጋ መሠረት፣ እንደ ገና አሳስባችሁ ዘንድ በአንዳንድ ጕዳዮች ላይ በድፍረት የጻፍሁላችሁ፣ በእግዚአብሔር ወንጌል የክህነት ተግባር፣ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ለመሆን ነው፤ ይኸውም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን በማገልገሌ በክርስቶስ ኢየሱስ እመካለሁ። በተናገርሁትና ባደረግሁት ነገር አሕዛብ ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ፣ ክርስቶስ በእኔ ሆኖ ከፈጸመው በቀር ሌላ ነገር ለመናገር አልደፍርም፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል፣ በምልክቶችና በታምራት ነበር። በዚህም ሁኔታ ከኢየሩሳሌም እስከ እልዋሪቆን ዙሪያ ድረስ የክርስቶስን ወንጌል ፈጽሜ ሰብኬአለሁ። ሌላው በጣለው መሠረት ላይ እንዳልገነባ ብዬ፣ ክርስቶስ ባልተጠራበት ስፍራ ወንጌልን መስበክ የዘወትር ምኞቴ ነበር። ይልቁንም፣ “ስለ እርሱ ያልተነገራቸው ያያሉ፤ ያልሰሙትም ያስተውላሉ” ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው። በዚህም ምክንያት ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ ተከለከልሁ። አሁን ግን በእነዚህ አካባቢዎች የምሠራው ስለሌለ፣ ከብዙ ዓመታት ጀምሮ እናንተን ለማየት እናፍቅም ስለ ነበር፣ ይህን ዕቅድ ወደ እስጳንያ በምሄድበት ጊዜ ልፈጽመው ዐስባለሁ። በማልፍበትም ጊዜ ልጐበኛችሁና ከእናንተ ጋራ ለጥቂት ጊዜ ቈይቼ ናፍቆቴን ከተወጣሁ በኋላ በጕዞዬ እንደምትረዱኝ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን ግን በዚያ የሚገኙትን ቅዱሳን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ላይ ነኝ። ምክንያቱም መቄዶንያና አካይያ፣ በኢየሩሳሌም ካሉት ቅዱሳን መካከል የሚገኙትን ድኾች ለመርዳት ተነሣሥተዋልና። ርዳታ ለማድረግ ወድደዋል፤ በርግጥም ባለዕዳዎቻቸው ናቸው። አሕዛብ የአይሁድ መንፈሳዊ በረከት ተካፋዮች ከሆኑ፣ ያገኙትን ምድራዊ በረከት ከአይሁድ ጋራ ይካፈሉ ዘንድ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናቸው። ስለዚህ ሥራውን ከጨረስሁና ይህን ፍሬ መቀበላቸውን ካረጋገጥሁ በኋላ ወደ እስጳንያ እሄዳለሁ፤ እግረ መንገዴንም እናንተን አያለሁ። ወደ እናንተም ስመጣ፣ በክርስቶስ በረከት ሙላት እንደምመጣ ዐውቃለሁ። ወንድሞች ሆይ፤ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የተጋድሎዬ አጋር እንድትሆኑ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ፍቅር እለምናችኋለሁ። በይሁዳ ካሉት ከማያምኑት እጅ እንድድንና በኢየሩሳሌም ያለው አገልግሎቴም በዚያ ባሉት ቅዱሳን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩልኝ፤ ይኸውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ እንድመጣና ከእናንተም ጋራ እንድታደስ ነው። የሰላም አምላክ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን። አሜን።

ሮሜ 15:5-33