የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

Psalms 98:1-9

መዝሙር 98:1-9 - ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤
እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤
ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም
ማዳንን አድርገውለታል።
እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤
ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።
ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣
ታማኝነቱንም ዐሰበ፤
የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣
የአምላካችንን ማዳን አዩ።

ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤
ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤
ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤
በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤
በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣
በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።

ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣
ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ።
ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፣
ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤
እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤
እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤
በዓለም ላይ በጽድቅ፣
በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።

ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤ እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም ማዳንን አድርገውለታል። እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ። ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ ታማኝነቱንም ዐሰበ፤ የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣ የአምላካችንን ማዳን አዩ። ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤ ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤ በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣ በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ። ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ፣ ዓለምና የሚኖሩባትም ሁሉ ያስገምግሙ። ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፣ ተራሮችም በአንድነት ይዘምሩ፤ እነዚህ በእግዚአብሔር ፊት ይዘምሩ፤ እርሱ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይበይናል።

መዝሙር 98:1-9

Psalms 98:1-9
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች