የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

Psalms 9:1-10

መዝሙር 9:1-10 - እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤
ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ።
በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤
ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ።

ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣
ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤
ፍርዴም ጕዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤
ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል።
ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤
ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።
ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤
ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤
መታሰቢያቸውም ተደምስሷል።

እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤
መንበሩንም ለፍርድ አጽንቷል።
ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤
ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።
እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤
በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።
ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

እግዚአብሔር ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም ሁሉ እናገራለሁ። በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤ ልዑል ሆይ፤ ስምህን በመዝሙር እወድሳለሁ። ጠላቶቼ ወደ ኋላ በተመለሱ ጊዜ፣ ተሰነካክለው ከፊትህ ይጠፋሉ፤ ፍርዴም ጕዳዬም በአንተ እጅ ናቸውና፤ ቅን ፍርድ እየሰጠህ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል። ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ። ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤ መታሰቢያቸውም ተደምስሷል። እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤ መንበሩንም ለፍርድ አጽንቷል። ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል። እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል። ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

መዝሙር 9:1-10

Psalms 9:1-10
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች