የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

Psalms 8:1-9

መዝሙር 8:1-9 - እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤
ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!

ክብርህ ከሰማያት በላይ፣
ከፍ ከፍ ብሏል።
ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣
ምስጋናን አዘጋጀህ፤
ከጠላትህ የተነሣ፣
ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ።
የጣቶችህን ሥራ፣
ሰማያትህን ስመለከት፣
በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣
ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣
በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤
ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው።
በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤
ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤
በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣
የዱር አራዊትንም፣
የሰማይ ወፎችንና
የባሕር ዓሦችን፣
በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።

እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤
ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!

እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው! ክብርህ ከሰማያት በላይ፣ ከፍ ከፍ ብሏል። ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣ ምስጋናን አዘጋጀህ፤ ከጠላትህ የተነሣ፣ ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ። የጣቶችህን ሥራ፣ ሰማያትህን ስመለከት፣ በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣ በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው። በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤ በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣ የዱር አራዊትንም፣ የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሦችን፣ በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት። እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!

መዝሙር 8:1-9

Psalms 8:1-9
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች