የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 40:1-8

መዝሙር 40:1-8 - እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤
እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።
ከሚውጥ ጕድጓድ፣
ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤
እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤
አካሄዴንም አጸና።
ለአምላካችን የሚሆን ውዳሴ፣
አዲስ ዝማሬን በአፌ ላይ አኖረ፤
ብዙዎች ያያሉ፤ ይፈራሉም፤
በእግዚአብሔር ይታመናሉ።

ብፁዕ ነው፤
እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣
ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣
የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፤
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤
አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤
ለእኛ ያቀድኸውን፣
ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤
ላውራው ልናገረው ብል፣
ስፍር ቍጥር አይኖረውም።

መሥዋዕትንና ቍርባንን አልፈለግህም፤
ጆሮዎቼን ግን ከፈትህ፤
የሚቃጠል መሥዋዕትን፣
የኀጢአትንም መሥዋዕት አልሻህም።
እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ መጥቻለሁ፤
ስለ እኔ በመጽሐፍ ተጽፏል፤
አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤
ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።”

እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ። ከሚውጥ ጕድጓድ፣ ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤ እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤ አካሄዴንም አጸና። ለአምላካችን የሚሆን ውዳሴ፣ አዲስ ዝማሬን በአፌ ላይ አኖረ፤ ብዙዎች ያያሉ፤ ይፈራሉም፤ በእግዚአብሔር ይታመናሉ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔርን መታመኛው ያደረገ፣ ወደ ትዕቢተኞች የማይመለከት፣ የሐሰት አማልክትን ወደሚከተሉት የማያይ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ ያደረግኸው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤ ለእኛ ያቀድኸውን፣ ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፣ ስፍር ቍጥር አይኖረውም። መሥዋዕትንና ቍርባንን አልፈለግህም፤ ጆሮዎቼን ግን ከፈትህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትን፣ የኀጢአትንም መሥዋዕት አልሻህም። እኔም እንዲህ አልሁ፤ “እነሆ፤ መጥቻለሁ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ተጽፏል፤ አምላኬ ሆይ፤ ፈቃድህን ላደርግ እሻለሁ፤ ሕግህም በልቤ ውስጥ አለ።”

መዝሙር 40:1-8

መዝሙር 40:1-8
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች