የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

Psalm 37:3-11

መዝሙር 37:3-11 - በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤
በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ።
በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤
የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።
መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤
በርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤
ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣
ፍትሕህን እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።
በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤
በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤
መንገዱ በተቃናለት፣
ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።

ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤
ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ።
ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ።

ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤
ስፍራውንም ብታሥሥ አታገኘውም።
ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤
በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

በእግዚአብሔር ታመን፤ መልካምንም አድርግ፤ በምድሪቱ ተቀመጥ፤ ዘና ብለህ ተሰማራ። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። መንገድህን ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ በርሱ ታመን፤ እርሱም ያከናውንልሃል፤ ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ ፍትሕህን እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል። በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር። ከንዴት ተቈጠብ፤ ቍጣንም ተወው፤ ወደ እኵይ ተግባር እንዳይመራህ አትከፋ። ክፉ ሰዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ። ለአፍታ እንጂ፣ ክፉ ሰው አይዘልቅም፤ ስፍራውንም ብታሥሥ አታገኘውም። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

መዝሙር 37:3-11

Psalm 37:3-11
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች