የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

Psalms 3:1-8

መዝሙር 3:1-8 - እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ!
ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ!
ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር
አይታደግሽም” አሏት። ሴላ

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤
ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ።
ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤
እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ

እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤
እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።
በየአቅጣጫው የከበበኝን፣
አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።

እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ!
አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤
የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤
የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።

ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤
በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ! ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት። ሴላ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ። ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ። በየአቅጣጫው የከበበኝን፣ አእላፍ ሕዝብ አልፈራም። እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ። ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ

መዝሙር 3:1-8

Psalms 3:1-8
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች