Psalms 3:1-8

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ ምንኛ በዙ! ስንቱስ በእኔ ላይ ተነሣ! ብዙዎች ነፍሴን፣ “እግዚአብሔር አይታደግሽም” አሏት። ሴላ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ዙሪያዬን የምትከልል ጋሻ ነህ፤ ክብሬንና ራሴንም ቀና ቀና የምታደርግ አንተ ነህ። ወደ እግዚአብሔር ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። ሴላ እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ። በየአቅጣጫው የከበበኝን፣ አእላፍ ሕዝብ አልፈራም። እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ። ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ
መዝሙር 3:1-8