አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ? አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም። አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤ የእስራኤልም ምስጋና ነህ። አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው። ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤ በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።
መዝሙር 22:1-5
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች