የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 22:1-9

መዝሙር 22:1-9 - አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?
እኔን ከማዳን፣
ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ?
አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
አንተ ግን አልመለስህልኝም፤
በሌሊት እንኳ አላረፍሁም።

አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤
የእስራኤልም ምስጋና ነህ።
አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤
ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው።
ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤
በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም።

እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤
ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ።
የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤
ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤
“በእግዚአብሔር ተማምኗል፤
እንግዲህ እርሱ ያድነው፤
ደስ የተሠኘበትን፣
እስኪ ይታደገው።”

አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤
በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።

አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳን፣ ከመቃተቴም ቃል ለምን ራቅህ? አምላኬ ሆይ፤ በቀን ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ አንተ ግን አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳ አላረፍሁም። አንተ ግን ቅዱሱ ነጋሢ፤ የእስራኤልም ምስጋና ነህ። አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው። ወደ አንተ ጮኹ፤ ዳኑም፤ በአንተም ታመኑ፤ አላፈሩም። እኔ ግን ትል እንጂ ሰው አይደለሁም፤ ሰው ያላገጠብኝ፣ ሕዝብም የናቀኝ ነኝ። የሚያዩኝ ሁሉ ይሣለቁብኛል፤ ራሳቸውንም እየነቀነቁ እንዲህ እያሉ ይዘልፉኛል፤ “በእግዚአብሔር ተማምኗል፤ እንግዲህ እርሱ ያድነው፤ ደስ የተሠኘበትን፣ እስኪ ይታደገው።” አንተ ግን ከማሕፀን አወጣኸኝ፤ በእናቴም ጡት ሳለሁ፣ መታመኛ ሆንኸኝ።

መዝሙር 22:1-9

መጽሐፈ መዝሙር 22:1-9
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች