የሚመክረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤
በሌሊት እንኳ ልቤ ቀናውን ያመላክተኛል።
እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤
እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።
ስለዚህ ልቤ ደስ አለው፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ፤
ሥጋዬም ያለ ሥጋት ዐርፎ ይቀመጣል፤
በሲኦል አትተወኝምና፤
በአንተ የታመነውም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።
የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤
በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣
በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።