እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣
ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።
በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣
አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤
በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣
“እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤
እኛም ደስ አለን።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣
ምርኳችንን መልስ።
በእንባ የሚዘሩ፣
በእልልታ ያጭዳሉ።
ዘር ቋጥረው፣
እያለቀሱ የተሰማሩ፣
ነዷቸውን ተሸክመው፣
እልል እያሉ ይመለሳሉ።