ሃሌ ሉያ።
በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣
ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
የእግዚአብሔር ሥራ ታላቅ ናት፤
ደስ የሚሰኙባትም ሁሉ ያውጠነጥኗታል።
ሥራው ባለክብርና ባለግርማ ነው፤
ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤
እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።
ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤
ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።
ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣
የአሠራሩን ብርታት አሳይቷል።