ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤
ትእዛዞቼን በልብህ ጠብቅ፤
ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤
ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል።
ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤
በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤
በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው።
በዚያ ጊዜ ሞገስንና ማስተዋልን፣
በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ።
በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፤
በራስህ ማስተዋል አትደገፍ፤
በመንገድህ ሁሉ እርሱን ዕወቅ፤
እርሱም ጐዳናህን ቀና ያደርገዋል።