Proverbs 18:1-24

ምሳሌ 18:1-24 - ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤
ቅን የሆነውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።

ሞኝ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤
የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።

ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤
ከዕፍረትም ጋራ ውርደት ትመጣለች።

ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤
የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

ለክፉ ሰው ማድላት፣
ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤
አፉም በትር ይጋብዛል።

ሞኝ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤
ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤
ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።

ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣
የአጥፊ ወንድም ነው።

የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤
ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤
እንደማይወጣ ረዥም ግንብም ይቈጥሩታል።

ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤
ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።

ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣
ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል።

በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤
የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?

የአስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይገበያል፤
የጠቢብም ጆሮ አጥብቆ ይሻታል።

እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤
ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።

አስቀድሞ ጕዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤
ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።

ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤
ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

የተበደለ ወንድም ከተመሸገ ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤
ጠቡም እንደ ጠንካራ የግንብ መዝጊያ ነው።

ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤
በከንፈሩም ምርት ይረካል።

አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤
የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።

ሚስት የሚያገኝ መልካም ነገርን ያገኛል፤
ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል።

ድኻ በመለማመጥ ምሕረት ይለምናል፤
ሀብታም ግን በማናለብኝነት ይመልሳል።

ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤
ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።

ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል። ሞኝ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤ የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል። ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ ከዕፍረትም ጋራ ውርደት ትመጣለች። ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤ የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው። ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም። የሞኝ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል። ሞኝ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው። የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል። ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣ የአጥፊ ወንድም ነው። የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል። የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ እንደማይወጣ ረዥም ግንብም ይቈጥሩታል። ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች። ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣ ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል። በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤ የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል? የአስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይገበያል፤ የጠቢብም ጆሮ አጥብቆ ይሻታል። እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች። አስቀድሞ ጕዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው። ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል። የተበደለ ወንድም ከተመሸገ ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤ ጠቡም እንደ ጠንካራ የግንብ መዝጊያ ነው። ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤ በከንፈሩም ምርት ይረካል። አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ። ሚስት የሚያገኝ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል። ድኻ በመለማመጥ ምሕረት ይለምናል፤ ሀብታም ግን በማናለብኝነት ይመልሳል። ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።

ምሳሌ 18:1-24