Micah 6:1-8

ሚክያስ 6:1-8 - እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ፤
“ተነሡ፤ ጕዳያችሁን በተራሮች ፊት አቅርቡ፤
ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ።

“ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤
እናንተ የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋራ ክርክር አለውና፤
ከእስራኤልም ጋራ ይፋረዳል።

“ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ?
ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው?
እስኪ መልስልኝ!
ከግብጽ አወጣሁህ፤
ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤
እንዲመሩህ ሙሴን፣
አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።
ሕዝቤ ሆይ፤
የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣
የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስኪ አስቡ፤
የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣
ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን ዐስቡ።”

ምን ይዤ በእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣
በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ?
የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣
ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋራ ይዤ በፊቱ ልቅረብን?
በአንድ ሺሕ አውራ በጎች፣
በዐሥር ሺሕ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን?
ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣
ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን?
ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤
እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?
ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣
በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ፤ “ተነሡ፤ ጕዳያችሁን በተራሮች ፊት አቅርቡ፤ ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ። “ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤ እናንተ የምድር ጽኑ መሠረቶችም፣ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋራ ክርክር አለውና፤ ከእስራኤልም ጋራ ይፋረዳል። “ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ? ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው? እስኪ መልስልኝ! ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤ እንዲመሩህ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ። ሕዝቤ ሆይ፤ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣ የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስኪ አስቡ፤ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣ ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን ዐስቡ።” ምን ይዤ በእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣ በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋራ ይዤ በፊቱ ልቅረብን? በአንድ ሺሕ አውራ በጎች፣ በዐሥር ሺሕ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን? ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣ ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን? ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

ሚክያስ 6:1-8

Micah 6:1-8