መልአኩም ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትፈልጉ ዐውቃለሁና፤ እርሱ በዚህ የለም፤ እንደ ተናገረው ተነሥቷል፤ ኑና ተኝቶበት የነበረውን ቦታ እዩ። አሁንም ፈጥናችሁ ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ፣ ‘ከሙታን ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል፤ በዚያ ታዩታላችሁ’ ብላችሁ ንገሯቸው። እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ!”
ሴቶቹም በፍርሀትና በደስታ ተሞልተው ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር በፍጥነት እየሮጡ የመቃብሩን ስፍራ ትተው ሄዱ።