Isaiah 9:1-21

ኢሳይያስ 9:1-21 - ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤
በጨለማ የሚኖር ሕዝብ
ታላቅ ብርሃን አየ፤
በሞት ጥላ ምድር ላሉትም
ብርሃን ወጣላቸው።
ሕዝብን አበዛህ፤
ደስታቸውንም ጨመርህ፤
ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣
ምርኮንም ሲከፋፈሉ
ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣
እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣
የከበዳቸውን ቀንበር፣
በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣
የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣
በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣
ለእሳት ይዳረጋል፤
ይማገዳልም።
ሕፃን ተወልዶልናል፤
ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።
ስሙም፣ ድንቅ መካር፣
ኀያል አምላክ፣
የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
ለመንግሥቱ ስፋት፣
ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣
መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤
ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።
በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤
አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት
ይህን ያደርጋል።
እግዚአብሔር
ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤
በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።
ሕዝቡ በሙሉ፣
ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች
ይህን ያውቃሉ፤
በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤
“ጡቦቹ ወድቀዋል፤
እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤
የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤
እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”
ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች አጠንክሯል፤
በርሱም ላይ ባላጋራዎቹን ያነሣሣበታል።
ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤
አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል።

በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤
እጁም እንደ ተነሣ ነው።

ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።
ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣
የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸንበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።
ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣
ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።
ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤
የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።
ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤
አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤
ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤
የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና።

በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤
እጁም እንደ ተነሣ ነው።

እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤
እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤
ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤
ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።
በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤
ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር
ማገዶ ይሆናል፤
ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም።
በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤
ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤
በግራም በኩል ይበላሉ፤
ነገር ግን አይጠግቡም፤
እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።
ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤
በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ።

ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤ በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ ምድር ላሉትም ብርሃን ወጣላቸው። ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል። ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል። የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም። ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል። ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል። እግዚአብሔር ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ይወድቃል። ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤ “ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።” ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች አጠንክሯል፤ በርሱም ላይ ባላጋራዎቹን ያነሣሣበታል። ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው። ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም። ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣ የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸንበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል። ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣ ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው። ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤ የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል። ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው። እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል። በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ትጋያለች፤ ሕዝቡም እሳት ውስጥ እንደሚጨመር ማገዶ ይሆናል፤ ወንድሙንም ማዳን የሚችል ማንም የለም። በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤ በግራም በኩል ይበላሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል። ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ።

ኢሳይያስ 9:1-21

Isaiah 9:1-21