የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 55:6-12

ኢሳይያስ 55:6-12 - እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤
ቀርቦም ሳለ ጥሩት።
ክፉ ሰው መንገዱን፣
በደለኛም ሐሳቡን ይተው።
ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤
ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

“ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣
መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”
ይላል እግዚአብሔር።

“ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣
መንገዴ ከመንገዳችሁ፣
ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።
ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣
ምድርን በማራስ፣
እንድታበቅልና እንድታፈራ
ለዘሪው ዘር፣
ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣
ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣
ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣
በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤
ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤
የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።
በደስታ ትወጣላችሁ፤
በሰላምም ትሸኛላችሁ፤
ተራሮችና ኰረብቶች፣
በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤
የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣
ያጨበጭባሉ።

እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት። ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና። “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና” ይላል እግዚአብሔር። “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣ መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው። ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣ ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል። በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኰረብቶች፣ በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤ የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ ያጨበጭባሉ።

ኢሳይያስ 55:6-12

ኢሳይያስ 55:6-12
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች