የYouVersion አርማ
መጽሐፍ ቅዱስእቅዶችቪዲዮዎች
መተግበሪያውን ያግኙ
የቋንቋ መምረጫ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 43:1-7

ኢሳይያስ 43:1-7 - አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣
እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤
በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤
በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣
ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤
ወንዙን ስትሻገረው፣
አያሰጥምህም፤
በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣
አያቃጥልህም፤
ነበልባሉም አይፈጅህም።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣
የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤
ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣
ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ።
ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣
እኔም ስለምወድድህ፣
ሰዎችን በአንተ ምትክ፣
ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ።
ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤
ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤
ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
ሰሜንን፣ ‘አምጣ!’
ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤
ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣
ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣
በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣
ለክብሬ የፈጠርሁትን፣
ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።”

አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤ በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም። እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤልም ቅዱስ መድኀኒትህ ነኝና፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ እንድትሆን፣ ኢትዮጵያንና ሳባን በአንተ ፈንታ እሰጣለሁ። ለዐይኔ ብርቅና ክቡርም ስለ ሆንህ፣ እኔም ስለምወድድህ፣ ሰዎችን በአንተ ምትክ፣ ሕዝቦችንም በሕይወትህ ፈንታ እሰጣለሁ። ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ ልጆችህን ከምሥራቅ አመጣለሁ፤ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። ሰሜንን፣ ‘አምጣ!’ ደቡብንም፣ ‘ልቀቅ’ እላለሁ፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣ በስሜ የተጠራውን ሁሉ፣ ለክብሬ የፈጠርሁትን፣ ያበጀሁትንና የሠራሁትን አምጡ።”

ኢሳይያስ 43:1-7

ኢሳይያስ 43:1-7
YouVersion

በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖርዎ እንዲፈልጉ የሚያበረታታዎ እና የሚሞግትዎ።

አገልግሎት

ስለ

ሙያዎች

በጎ ፈቃደኛ

ብሎግ

ተጫን / ይንኩት

ጠቃሚ ማስፈንጠሪያዎች

እገዛ

ልገሳ

የመጽሐፍ ቅዱስ እትሞች

የድምጽ መጽሐፍ ቅዱስ

የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች

የዕለቱ ጥቅስ


የዲጂታል አገልግሎት

Life.Church
English (US)

©2025 Life.Church / YouVersion

የግለሰብነት መመሪያ / የግለሰብ አቋም መመሪያውሎች
የተጋላጭነት ገለጻ ፕሮግራም
ፌስቡክትዊተርኢንስታግራምዩትዩብፒንትረስት

ቤት

መጽሐፍ ቅዱስ

እቅዶች

ቪዲዮዎች