ኢሳይያስ 41:10-20

ኢሳይያስ 41:10-20 - እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤
አምላክህ ነኝና አትደንግጥ።
አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤
በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

“እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣
እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤
የሚቋቋሙህ፣
እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።
ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣
አታገኛቸውም፤
የሚዋጉህም፣
እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤
እረዳሃለሁ።
አንተ ትል ያዕቆብ፣
ታናሽ እስራኤል ሆይ፤
‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤
የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
“እነሆ፣ አዲስ
የተሳለና ባለጥርስ ማሄጃ አደርግሃለሁ፤
ተራሮችን ታሄዳለህ፤ ታደቅቃቸዋለህ፤
ኰረብቶችንም ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
ታበጥራቸዋለህ፤ ነፋስ ጠርጎ ይወስዳቸዋል፤
ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል።
አንተ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤
በእስራኤል ቅዱስ ሞገስ ታገኛለህ።

“ድኾችና ችግረኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤
ዳሩ ግን ምንም አያገኙም፤
ጕረሯቸው በውሃ ጥም ደርቋል።
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እመልስላቸዋለሁ፤
እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም።
በተራቈቱ ኰረብቶች ላይ ወንዞችን፣
በሸለቆዎች ውስጥ ምንጮችን አፈልቃለሁ።
ምድረ በዳውን የውሃ ኵሬ፣
የተጠማውን ምድር የውሃ ምንጭ አደርጋለሁ።
በምድረ በዳ፣
ዝግባን፣ ግራርን፣ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤
በበረሓ፣ ጥድን፣ አስታንና
ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ።
ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤
የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣
የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣
በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም።

እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ። “እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣ እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ የሚቋቋሙህ፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም። ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣ አታገኛቸውም፤ የሚዋጉህም፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ። እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ። አንተ ትል ያዕቆብ፣ ታናሽ እስራኤል ሆይ፤ ‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው። “እነሆ፣ አዲስ የተሳለና ባለጥርስ ማሄጃ አደርግሃለሁ፤ ተራሮችን ታሄዳለህ፤ ታደቅቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ገለባ ታደርጋቸዋለህ። ታበጥራቸዋለህ፤ ነፋስ ጠርጎ ይወስዳቸዋል፤ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በእስራኤል ቅዱስ ሞገስ ታገኛለህ። “ድኾችና ችግረኞች ውሃ ይፈልጋሉ፤ ዳሩ ግን ምንም አያገኙም፤ ጕረሯቸው በውሃ ጥም ደርቋል። ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እመልስላቸዋለሁ፤ እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም። በተራቈቱ ኰረብቶች ላይ ወንዞችን፣ በሸለቆዎች ውስጥ ምንጮችን አፈልቃለሁ። ምድረ በዳውን የውሃ ኵሬ፣ የተጠማውን ምድር የውሃ ምንጭ አደርጋለሁ። በምድረ በዳ፣ ዝግባን፣ ግራርን፣ ባርሰነትንና ወይራን አበቅላለሁ፤ በበረሓ፣ ጥድን፣ አስታንና ሸውሸዌን በአንድነት እተክላለሁ። ስለዚህ ሰዎች ያያሉ፤ ያውቃሉ፤ የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፣ የእስራኤል ቅዱስ እንደ ፈጠረው፣ በአንድነት ይገነዘባሉ፤ ያስተውላሉም።

ኢሳይያስ 41:10-20