Isaiah 25:8-12

ሞትንም ለዘላለም ይውጣል። ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ውርደት ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሯልና። በዚያ ቀን እንዲህ ይባላል፤ “እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በርሱ ታመንን፤ በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።” የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤ ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋራ እንደሚረገጥ፣ ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል። ዋናተኛ ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፣ በውስጡ ሆነው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ ጌታ በእጃቸው ተንኰል ሳይታለል፣ ትዕቢታቸውን ያዋርዳል። ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤ ወደ ታች ያወርደዋል፤ ወደ ምድር አውርዶም ትቢያ ላይ ይጥለዋል።
ኢሳይያስ 25:8-12