በዚያ ቀን እንዲህ ትላለህ፤
“እግዚአብሔር ሆይ፤
ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤
አሁን ግን ከቍጣህ ተመለስህ፤
ደግሞም አጽናንተኸኛልና አወድስሃለሁ።
እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤
እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤
ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤
ድነቴም ሆኗል።”
ከድነቴ ምንጮች
ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።
በዚያ ቀን እንዲህ ትላላችሁ፤
“እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤
ያደረገውንም በአሕዛብ መካከል አስታውቁ፤
ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱንም ዐውጁ።