የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ romans 6:23

ሮሜ 6:23 (NASV)

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ዘፀአት 6:23 (NASV)

አሮንም የአሚናዳብን ልጅ፣ የነአሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፤ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ወለደችለት።

ዘሌዋውያን 6:23 (NASV)

ካህኑ የሚያቀርበው የእህል ቍርባን ሁሉ ፈጽሞ ይቃጠል እንጂ አይበላ።”

ዘኍልቍ 6:23 (NASV)

“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘እስራኤላውያንን በምትባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሏቸው፤

ዘዳግም 6:23 (NASV)

እኛን ግን ለአባቶቻችን በመሐላ ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ሊያስገባንና ሊሰጠን ከዚያ አወጣን።

ኢያሱ 6:23 (NASV)

ስለዚህ ሁለቱ ወጣት ሰላዮች ገብተው ረዓብን፣ አባቷንና እናቷን፣ ወንድሞቿንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ ከዚያ አወጧቸው። ቤተ ዘመዶቿንም ሁሉ አውጥተው ከእስራኤል ሰፈር ውጭ አስቀመጧቸው።

መሳፍንት 6:23 (NASV)

እግዚአብሔር ም፣ “ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አትፍራ፤ አትሞትም” አለው።

ኤፌሶን 6:23 (NASV)

ከእግዚአብሔር አብ፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም፣ ፍቅርም ከእምነት ጋራ ለወንድሞች ይሁን።

ኢዮብ 6:23 (NASV)

ወይስ፣ ‘ከጠላት አስጥሉኝ፣ ከጨካኝም እጅ ተቤዡኝ’ አልኋችሁን?

ምሳሌ 6:23 (NASV)

እነዚህ ትእዛዞች መብራት ናቸውና፤ ይህችም ትምህርት ብርሃን፣ የተግሣጽ ዕርምትም የሕይወት መንገድ ናት፤

ኤርምያስ 6:23 (NASV)

ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞችና ምሕረት የለሽ ናቸው፤ ፈረሶቻቸውን ሲጋልቡ፣ ድምፃቸው እንደ ተናወጠ ባሕር ነው፤ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ለሰልፍ የታጠቁ ሆነው፣ ሊወጉሽ ይመጣሉ።”

ዳንኤል 6:23 (NASV)

ንጉሡ እጅግ ተደስቶ፤ ዳንኤልን ከጕድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ። ዳንኤል በአምላኩ ታምኖ ነበርና ከጕድጓድ በወጣ ጊዜ፣ አንዳች ጕዳት አልተገኘበትም።

ማቴዎስ 6:23 (NASV)

ዐይንህ ታማሚ ከሆነ ግን መላው ሰውነትህ በጨለማ የተሞላ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ድቅድቅ ይሆን?

ማርቆስ 6:23 (NASV)

ደግሞም “እስከ መንግሥቴ እኩሌታ ድረስ እንኳ ቢሆን፣ የምትጠይቂኝን ሁሉ እሰጥሻለሁ” ሲል በመሐላ ቃል ገባላት።

ሉቃስ 6:23 (NASV)

“እነሆ፤ ወሮታችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፣ በዚያ ቀን ደስ ይበላችሁ፤ ፈንድቁም፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነበርና።

ዮሐንስ 6:23 (NASV)

ከዚያም በኋላ፣ ሌሎች ጀልባዎች ከጥብርያዶስ ሕዝቡ ጌታ የባረከውን እንጀራ ወደ በላበት ስፍራ መጡ።

2 ሳሙኤል 6:23 (NASV)

የሳኦልም ልጅ ሜልኮል እስከሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር።

1 ነገሥት 6:23 (NASV)

በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ሁለት የኪሩቤል ቅርጽ ከወይራ ዕንጨት ሠራ፤

2 ነገሥት 6:23 (NASV)

ስለዚህ ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶላቸው ከበሉና ከጠጡ በኋላ አሰናብቷቸው ወደ ጌታቸው ሄዱ። የሶርያ አደጋ ጣዮችም የእስራኤልን ምድር ለመውረር ከዚያ በኋላ አልተመለሱም።

1 ዜና መዋዕል 6:23 (NASV)

ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ አብያሳፍ፣ ልጁ አሴር፣

2 ዜና መዋዕል 6:23 (NASV)

ከሰማይ ሆነህ ስማ፤ አድርግም። በደለኛውን፣ በደሉን በራሱ ላይ አድርገህ እንደ ሥራው በመክፈል በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ። ንጹሑም በደለኛ አለመሆኑን አስታውቅ፤ እንደ ንጽሕናውም ክፈለው።

ዘፍጥረት 23:6 (NASV)

“ስማን ጌታዬ፤ አንተ እኮ በእኛ ዘንድ እንደ ኀያል መስፍን ነህ፤ ከመቃብር ቦታችን በመረጥኸው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፤ ማንኛችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የመቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።”

ዘፀአት 23:6 (NASV)

“በዳኝነት ጊዜ በድኻው ላይ ፍርድ አታጓድልበት።

ዘሌዋውያን 23:6 (NASV)

በዚያው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን የ እግዚአብሔር የቂጣ በዓል ይጀመራል፤ ለሰባት ቀንም ቂጣ ብሉ።

ዘኍልቍ 23:6 (NASV)

እርሱም ተመልሶ ሲሄድ ባላቅን ከመላው የሞዓብ አለቆች ጋራ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አገኘው።