የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ genesis 1:27
1 ሳሙኤል 27:1 (NASV)
ዳዊት ግን በልቡ፣ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፣ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ ዐሰበ።
1 ሳሙኤል 27:2 (NASV)
ስለዚህ ዳዊትና ዐብረውት ያሉት ስድስት መቶ ሰዎች ተነሥተው የጋት ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ሄዱ።
1 ሳሙኤል 27:3 (NASV)
ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአንኩስ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተ ሰቡ ጋራ ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋራ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢግያ ጋራ ነበር።
1 ሳሙኤል 27:4 (NASV)
ሳኦልም፣ ዳዊት ወደ ጋት እንደ ሸሸ በሰማ ጊዜ፣ እርሱን ማሳደዱን ተወ።
1 ሳሙኤል 27:5 (NASV)
ከዚያም ዳዊት አንኩስን፣ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ እኖር ዘንድ ስፍራ ይሰጠኝ፤ ስለ ምን አገልጋይህ ካንተ ጋራ በንጉሥ ከተማ ይቀመጣል?” አለው።
1 ሳሙኤል 27:6 (NASV)
ስለዚህ በዚያ ዕለት አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ ጺቅላግም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ ሆነች።
1 ሳሙኤል 27:7 (NASV)
ዳዊት በፍልስጥኤማውያን ምድር አንድ ዓመት ከአራት ወር ተቀመጠ።
1 ሳሙኤል 27:8 (NASV)
በዚያ ጊዜም ዳዊትና ሰዎቹ ወጥተው ጌሹራውያንን፣ ጌርዛውያንንና አማሌቃውያንን ወረሩ። እነዚህ ሕዝቦች ከጥንት ጀምሮ፣ እስከ ሱርና እስከ ግብጽ ባለው ምድር ላይ ይኖሩ ነበር።
1 ሳሙኤል 27:9 (NASV)
ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ ነገር ግን በጎችንና ላሞችን፣ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አንኩስም ተመለሰ።
1 ሳሙኤል 27:10 (NASV)
አንኩስም፣ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፣ “የዘመትነው በይሁዳ ደቡብ፣ ወይም በይረሕምኤላውያን ደቡብ፣ ወይም በቄናውያን ደቡብ ላይ ነው” በማለት ይመልስ ነበር።
1 ሳሙኤል 27:11 (NASV)
ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፣ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ፣ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።
1 ሳሙኤል 27:12 (NASV)
አንኩስም በልቡ፣ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፣ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።
1 ዜና መዋዕል 27:1 (NASV)
የእስራኤል የቤተ ሰብ አለቆች፣ የሻለቆች፣ የመቶ አለቆች እንዲሁም ዓመቱን ሙሉ በየወሩ የሚመደቡትን ዋና ዋና ክፍሎች በተመለከተ ንጉሡን ያገለገሉ አለቆቻቸው ዝርዝር ይህ ነው። እያንዳንዱ ዋና ክፍል ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረው።
1 ዜና መዋዕል 27:2 (NASV)
በመጀመሪያው ወር፣ የመጀመሪያው ዋና ክፍል የበላይ የዘብድኤል ልጅ ያሾብዓም ሲሆን፣ በሥሩ የሚታዘዙ ሃያ አራት ሺሕ ሰዎች ነበሩ።
1 ዜና መዋዕል 27:3 (NASV)
እርሱም የፋሬስ ዘር ሲሆን፣ በመጀመሪያው ወር የሰራዊቱ ሹማምት ሁሉ የበላይ ነበር።
1 ዜና መዋዕል 27:4 (NASV)
በሁለተኛው ወር፣ የክፍለ ጦሩ የበላይ አዛዥ አሆሃዊው ዱዲ ሲሆን፣ የዚሁ ክፍል መሪ ደግሞ ሚቅሎት ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:5 (NASV)
በሦስተኛውም ወር፣ የሦስተኛው ክፍለ ጦር የበላይ አዛዥ የካህኑ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ነበረ፤ ዋናው እርሱ ሲሆን፣ በሥሩ ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:6 (NASV)
ይህም በናያስ ከሠላሳዎቹ ይልቅ ኀያል ሲሆን፣ የሠላሳዎቹ የበላይ ነበረ፤ ልጁ ዓሚዛ ባድም የክፍሉ ሰራዊት አዛዥ ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:7 (NASV)
በአራተኛው ወር፣ አራተኛው የበላይ አዛዥ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል ሲሆን፣ በእግሩ የተተካውም ልጁ ዝባድያ ነው፤ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:8 (NASV)
በዐምስተኛው ወር፣ ዐምስተኛው የበላይ አዛዥ ይዝራዊው ሸምሁት ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:9 (NASV)
በስድስተኛው ወር፣ ስድስተኛው የበላይ አዛዥ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:10 (NASV)
በሰባተኛው ወር፣ ሰባተኛው የበላይ አዛዥ የኤፍሬም ወገን የሆነው ፍሎናዊው ሴሌስ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:11 (NASV)
በስምንተኛው ወር፣ ስምንተኛው የበላይ አዛዥ ከካዛራውያን ወገን የሆነው ኩሳታዊው ሴቦካይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:12 (NASV)
በዘጠነኛው ወር፣ ዘጠነኛው የበላይ አዛዥ ከብንያም ወገን የሆነው ዓናቶታዊው አቢዔዜር ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 27:13 (NASV)
በዐሥረኛው ወር፣ ዐሥረኛው የበላይ አዛዥ ከዛራውያን ወገን የሆነው ነጦፋዊው ማህራይ ሲሆን፣ በሥሩም ሃያ አራት ሺሕ ሰው ነበረ።