የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ Romans 3:23
ሮሜ 3:23 (NASV)
ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሏቸዋል፤
ቈላስይስ 3:23 (NASV)
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት ቈጥራችሁ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት፤
ነህምያ 3:23 (NASV)
ከእነርሱ ቀጥሎ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መልሰው ሠሩ፤ ከእነርሱም ቀጥሎ የሐናንያ ልጅ የመዕሤያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን መልሶ ሠራ።
ኢዮብ 3:23 (NASV)
መንገዱ ለተሰወረበት ሰው፤ እግዚአብሔርም በዐጥር ላጠረው፣ ሕይወት ለምን ተሰጠ?
ምሳሌ 3:23 (NASV)
ከዚያም መንገድህን ያለ ሥጋት ትሄዳለህ፤ እግርህም አይሰናከልም፤
ኢሳይያስ 3:23 (NASV)
መስተዋቱን፣ ከጥሩ በፍታ የተሠራውን ልብስ፣ የራስ ጌጡን፣ ዐይነ ርግቡን ሁሉ ይነጥቃቸዋል።
ኤርምያስ 3:23 (NASV)
በርግጥ በኰረብቶች ላይ፣ እንዲሁም በተራሮች ላይ፣ ሆ! ብለን መውጣታችን መታለል ነው፤ በርግጥ የእስራኤል መዳን፣ በአምላካችን በ እግዚአብሔር ነው።
ሰቈቃወ 3:23 (NASV)
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህም ብዙ ነው።
ሕዝቅኤል 3:23 (NASV)
እኔም ተነሥቼ ወደ ረባዳው ስፍራ ሄድሁ። በኮቦር ወንዝ አጠገብ ያየሁት ዐይነት ክብር፣ የ እግዚአብሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፤ እኔም በግንባሬ ተደፋሁ።
ዳንኤል 3:23 (NASV)
ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ ግን ተጠፍረው እንደ ታሰሩ በሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ወደቁ።
ማርቆስ 3:23 (NASV)
እርሱም ጠራቸውና በምሳሌ እንዲህ አላቸው፤ “ሰይጣን ሰይጣንን እንዴት ሊያስወጣ ይችላል?
ሉቃስ 3:23 (NASV)
ኢየሱስ አገልግሎቱን ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ነበር፤ ሕዝቡም እንደ መሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፦ የኤሊ ልጅ፣
ዮሐንስ 3:23 (NASV)
በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ለመጠመቅ ይመጡ ነበር።
ዘፍጥረት 3:23 (NASV)
ስለዚህ የተገኘበትን ምድር እንዲያርስ፣ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከዔድን የአትክልት ስፍራ አስወጣው፤
ዘኍልቍ 3:23 (NASV)
የጌርሶን ጐሣዎች በምዕራብ በኩል ከማደሪያው ድንኳን ጀርባ ይሰፍራሉ።
ዘዳግም 3:23 (NASV)
በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር ን እንዲህ ብዬ ለመንሁት፤
መሳፍንት 3:23 (NASV)
ከዚያም በኋላ ናዖድ በዕልፍኙ መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው።
ገላትያ 3:23 (NASV)
ይህ እምነት ከመምጣቱ በፊት በሕግ አማካይነት እስረኞች ሆነን፣ እምነት እስከሚገለጥ ድረስ ተዘግቶብን ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 3:23 (NASV)
ያን ነቢይ የማትሰማ ነፍስ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይታ ትጥፋ።’
2 ሳሙኤል 3:23 (NASV)
ኢዮአብና ዐብሮት የነበረው ሰራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፣ የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መምጣቱን፣ ንጉሡ እንዳሰናበተውና እርሱም በሰላም እንደ ሄደ፣ ኢዮአብ ሰማ።
1 ነገሥት 3:23 (NASV)
ንጉሡም፣ “ይህችኛዪቱ፣ ‘የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው፣ የአንቺ የሞተው ነው’ ትላለች፤ ያችኛዪቱ ደግሞ፣ ‘አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቷል፣ በሕይወት ያለው የእኔ ነው’ ትላለች” አለ።
2 ነገሥት 3:23 (NASV)
ስለዚህ፣ “ያ እኮ ደም ነው! ያለ ጥርጥር ነገሥታቱ እርስ በርስ ተዋግተው ተራርደዋል። እንግዲህ ሞዓብ ወደ ምርኮህ ዙር!” ተባባሉ።
1 ቆሮንቶስ 3:23 (NASV)
እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
1 ዮሐንስ 3:23 (NASV)
ትእዛዙም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና እርሱ እንዳዘዘንም እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው።
1 ዜና መዋዕል 3:23 (NASV)
የነዓርያ ወንዶች ልጆች፤ ኤልዮዔናይ፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዝሪቃም፤ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።