የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ Luke 8:30
ዕዝራ 8:30 (NASV)
ከዚያም ካህናቱና ሌዋውያኑ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ አምላካችን ቤት እንዲሄድ የተመዘነውን ብር፣ ወርቅና ንዋያተ ቅድሳት ተረከቡ።
ምሳሌ 8:30 (NASV)
በዚያ ጊዜ ከጐኑ ዋና ባለሙያ ነበርሁ። ሁልጊዜ በፊቱ ሐሤት እያደረግሁ፣ ዕለት ተዕለት በደስታ እሞላ ነበር፤
ማቴዎስ 8:30 (NASV)
ከእነርሱ ትንሽ ራቅ ብሎ፣ የብዙ ዐሣማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።
ማርቆስ 8:30 (NASV)
ኢየሱስም ስለ እርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው።
ሉቃስ 8:30 (NASV)
ኢየሱስም፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ስለ ነበር፣ “ሌጌዎን” አለው።
ዮሐንስ 8:30 (NASV)
ይህንም እንደ ተናገረ ብዙዎች በርሱ አመኑ።
ዘፀአት 8:30 (NASV)
ከዚያም ሙሴ ከፈርዖን ተለይቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
ዘሌዋውያን 8:30 (NASV)
ቀጥሎም ሙሴ በመቅቢያው ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ደም ጥቂት ወስዶ፣ በአሮንና በልብሱ እንዲሁም በአሮን ልጆችና በልብሳቸው ላይ ረጨ፤ በዚህም ሁኔታ አሮንንና ልብሱን፣ ልጆቹንና ልብሳቸውን ቀደሰ።
ኢያሱ 8:30 (NASV)
ከዚያም ኢያሱ በጌባል ተራራ ላይ ለእስራኤል አምላክ ለ እግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
መሳፍንት 8:30 (NASV)
ጌዴዎን ብዙ ሚስቶች ስላገባ ሰባ ልጆች ነበሩት፤
ሮሜ 8:30 (NASV)
አስቀድሞ የወሰናቸውንም ጠራቸው፤ የጠራቸውንም አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም አከበራቸው።
ሐዋርያት ሥራ 8:30 (NASV)
ፊልጶስም ፈጥኖ ወደ ሠረገላው ሄደ፤ ጃንደረባውም የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብብ ሰምቶ፣ “ለመሆኑ፣ የምታነብበውን ታስተውለዋለህን?” አለው።
1 ነገሥት 8:30 (NASV)
ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ ጸሎት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ልመናቸውን ተቀበል፤ መኖሪያህ በሆነው በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።
1 ዜና መዋዕል 8:30 (NASV)
የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ጹር፣ ቂስ፣ ባኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣
ኢዮብ 30:8 (NASV)
ስማቸው የማይታወቅ ሞኞች ናቸው፤ ከምድሪቱም ተባርረዋል።
መዝሙር 30:8 (NASV)
እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ ተጣራሁ፤ ወደ ጌታም እንዲህ ብዬ ጮኽሁ፤
ምሳሌ 30:8 (NASV)
ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ።
ኢሳይያስ 30:8 (NASV)
አሁንም ሂድ፤ በሰሌዳ ላይ ጻፍላቸው፤ በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ክተብላቸው፤ ለሚመጡትም ዘመናት፣ ለዘላለም ምስክር ይሆናል፤
ኤርምያስ 30:8 (NASV)
“ ‘በዚያ ቀን’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ፤ ‘በጫንቃቸው ላይ ያለውን ቀንበር እሰብራለሁ፤ እስራታቸውንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህ ባዕዳን አይገዟቸውም።
ሕዝቅኤል 30:8 (NASV)
በግብጽ ላይ እሳት ስጭር፣ ረዳቶቿ ሁሉ ሲደቅቁ፣ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ዘፍጥረት 30:8 (NASV)
ራሔልም፣ “እኅቴን ብርቱ ትግል ገጥሜ አሸነፍሁ” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ አወጣችለት።
ዘፀአት 30:8 (NASV)
ምሽት ላይ መብራቶቹን በሚያበራበትም ጊዜ ዕጣኑን ማጠን አለበት፤ ይኸውም በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ዕጣኑ በ እግዚአብሔር ፊት ዘወትር እንዲጤስ ነው።
ዘኍልቍ 30:8 (NASV)
ሆኖም ባሏ ይህንኑ ሰምቶ ከከለከላት ግን ለመፈጸም የተሳለችውንም ሆነ አምልጧት ተናግራ ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ነገር ስለሚያስቀር እግዚአብሔር ከዚህ ነጻ ያደርጋታል።
ዘዳግም 30:8 (NASV)
አንተም ተመልሰህ ለ እግዚአብሔር ትታዘዛለህ፤ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቃለህ።
1 ሳሙኤል 30:8 (NASV)
ዳዊትም፣ “ይህን ወራሪ ሰራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል እግዚአብሔር ን ጠየቀ። እግዚአብሔር ም፣ “በርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተል” ሲል መለሰለት።