የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ John 3:16

ቈላስይስ 3:16 (NASV)

የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።

ዮሐንስ 3:16 (NASV)

በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።

2 ጢሞቴዎስ 3:16 (NASV)

ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤

ዘፍጥረት 3:16 (NASV)

ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”

ዘፀአት 3:16 (NASV)

“ሂድና የእስራኤልን አለቆች ሰብስበህ፣ ‘የአባቶቻችሁ የአብርሃም፣ የይሥሐቅና የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፤ ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብጽ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ።

ዘሌዋውያን 3:16 (NASV)

ካህኑም ይህን ሁሉ በእሳት የሚቀርብና ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ሥብ ሁሉ የ እግዚአብሔር ነው።

ዘኍልቍ 3:16 (NASV)

ስለዚህ ሙሴ በ እግዚአብሔር ቃል በታዘዘው መሠረት እነዚህን ቈጠራቸው።

ዘዳግም 3:16 (NASV)

ነገር ግን የሸለቆውን እኩሌታ ወሰን በማድረግ ከገለዓድ አንሥቶ እስከ አርኖን ሸለቆ፣ ከዚያም የአሞናውያን ድንበር እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ያለውን ግዛት ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።

ኢያሱ 3:16 (NASV)

ከላይ የሚወርደው ውሃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ “አዳም” ተብላ እስከምትጠራው ሩቅ ከተማ ድረስ በመከማቸት እንደ ክምር ተቈለለ፤ ቍልቍል ወደ ዓረባ ጨው ባሕር የሚወርደውም ውሃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም ከኢያሪኮ ትይዩ ባለው አቅጣጫ ተሻገሩ።

መሳፍንት 3:16 (NASV)

እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው።

ሩት 3:16 (NASV)

ሩት ወደ ዐማቷ እንደ ተመለሰች፣ ኑኃሚን፣ “ልጄ ሆይ፤ የሄድሽበት ጕዳይ እንዴት ሆነ?” ብላ ጠየቀቻት። ሩትም ቦዔዝ ያደረገላትን ሁሉ ነገረቻት፤

ሮሜ 3:16 (NASV)

በመንገዶቻቸው ጥፋትና ጕስቍልና ይገኛሉ፤

ገላትያ 3:16 (NASV)

የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር፤ መጽሐፍ፣ ለብዙ ሰዎች እንደሚነገር፣ “ለዘሮቹ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ ሰው እንደሚነገር፣ “ለዘርህ” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።

ኤፌሶን 3:16 (NASV)

በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤

ፊልጵስዩስ 3:16 (NASV)

ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ።

ዕብራውያን 3:16 (NASV)

ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብጽ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?

ያዕቆብ 3:16 (NASV)

ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ።

ራእይ 3:16 (NASV)

እንግዲህ ለብ ያልህ ብቻ እንጂ ትኵስ ወይም ቀዝቃዛ ስላልሆንህ ከአፌ አውጥቼ ልተፋህ ነው።

ነህምያ 3:16 (NASV)

ከርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዥ የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ እስከ ዳዊት መቃብር ትይዩ እስከ ሰው ሠራሹ ኵሬና የጀግኖች ቤት ተብሎ እስከሚጠራው ድረስ ያለውን መልሶ ሠራ።

ኢዮብ 3:16 (NASV)

ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፣ ብርሃንም እንዳላየ ሕፃን በሆንሁ ነበር።

ምሳሌ 3:16 (NASV)

በቀኝ እጇ ረዥም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇም ሀብትና ክብር ይዛለች።

መክብብ 3:16 (NASV)

ከፀሓይ በታችም ሌላ ነገር አየሁ፤ በፍርድ ቦታ ዐመፅ ነበር፤ በፍትሕ ቦታ ግፍ ነበር።

ኢሳይያስ 3:16 (NASV)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፣ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፣ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።

ኤርምያስ 3:16 (NASV)

ቍጥራችሁ በምድሪቱ እጅግ በሚበዛበት ጊዜም” ይላል እግዚአብሔር ፤ “በዚያ ዘመን፣ ‘የ እግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት’ ብለው ከእንግዲህ አይጠሩም፤ ትዝ አይላቸውም፤ አያስታውሱትምም፤ አይጠፋም፤ ሌላም አይሠራም።

ሰቈቃወ 3:16 (NASV)

ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፤ በትቢያ ውስጥ ረጋገጠኝ።