የፍለጋ ውጤቶች ለ፦ 1 Samuel 15
1 ሳሙኤል 15:1 (NASV)
ሳሙኤል ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ቀብቼ እንዳነግሥህ፣ እግዚአብሔር የላከው እኔን ነው፤ ስለዚህ የ እግዚአብሔር ን ድምፅ አሁን ስማ።
1 ሳሙኤል 15:2 (NASV)
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ፣ አማሌቃውያን በመንገድ ላይ ስለ ተቃወሙት እቀጣቸዋለሁ።
1 ሳሙኤል 15:3 (NASV)
አሁንም ሂድ፤ አማሌቃውያንን ውጋ፤ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፤ አንዱንም አታስቀር፤ ወንዱንና ሴቱን፣ ልጁንና ሕፃኑን፣ የቀንድ ከብቱንና በጉን፣ ግመሉንና አህያውን ግደል።’ ”
1 ሳሙኤል 15:4 (NASV)
ስለዚህ ሳኦል ሰዎቹን ጥላኢም በተባለ ቦታ ሰብስቦ ቈጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺሕ እግረኛ ወታደሮችና ከይሁዳም ዐሥር ሺሕ ሰዎች ነበሩ፤
1 ሳሙኤል 15:5 (NASV)
ሳኦልም ወደ አማሌቅ ከተማ ሄዶ በአንዲት ሸለቆ ውስጥ አደፈጠ።
1 ሳሙኤል 15:6 (NASV)
እርሱም፣ ቄናውያንን፣ “ከእነርሱ ጋራ እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ፣ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።
1 ሳሙኤል 15:7 (NASV)
ከዚያም ሳኦል አማሌቃውያንን ከኤውላጥ አንሥቶ በምሥራቅ ግብጽ እስካለው እስከ ሱር ድረስ ወጋቸው።
1 ሳሙኤል 15:8 (NASV)
የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
1 ሳሙኤል 15:9 (NASV)
ነገር ግን ሳኦልና ሰራዊቱ አጋግን፣ ምርጥ ምርጡን በግና የቀንድ ከብት፣ የሰባውን ጥጃና ጠቦት፣ መልካም የሆነውን ሁሉ ሳይገድሉ ተውት። እነዚህን ፈጽመው ለማጥፋት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ ነገር ግን የተናቀውንና የማይጠቅመውን ሁሉ አጠፉ።
1 ሳሙኤል 15:10 (NASV)
ከዚህ በኋላ የ እግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፤
1 ሳሙኤል 15:11 (NASV)
“ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ፤ እኔን ከመከተል ተመልሷልና፣ ትእዛዜንም አልፈጸመምና።” ሳሙኤልም እጅግ ተጨንቆ፣ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
1 ሳሙኤል 15:12 (NASV)
ሳሙኤልም ጧት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፣ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።
1 ሳሙኤል 15:13 (NASV)
ሳሙኤል ባገኘው ጊዜ ሳኦል፣ “ እግዚአብሔር ይባርክህ፤ የ እግዚአብሔር ን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ” አለው።
1 ሳሙኤል 15:14 (NASV)
ሳሙኤል ግን፣ “ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ጩኸትና የበሬዎች ግሣት ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ።
1 ሳሙኤል 15:15 (NASV)
ሳኦልም፣ “ሰራዊቱ ከአማሌቃውያን ማርከው ያመጧቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጦቹ በጎችና በሬዎች ለ እግዚአብሔር ለአምላክህ መሥዋዕት እንዲሆኑ ሳይገድሉ የተዉአቸው ናቸው፤ የቀሩትን ግን በሙሉ አጥፍተናል” ብሎ መለሰ።
1 ሳሙኤል 15:16 (NASV)
ሳሙኤልም ሳኦልን፣ “ስማ! ትናንት ማታ እግዚአብሔር የነገረኝን ልንገርህ?” አለው። ሳኦልም፣ “ንገረኝ” ሲል መለሰለት።
1 ሳሙኤል 15:17 (NASV)
ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “በዐይንህ ፊት ታናሽ የነበርህ ብትሆንም፣ የእስራኤል ነገዶች መሪ ሆነህ የለምን? እግዚአብሔር ም በእስራኤል ላይ ቀብቶ አንግሦሃል።
1 ሳሙኤል 15:18 (NASV)
እግዚአብሔርም፣ ‘ሄደህ እነዚያን ኀጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ጨርሰህ እስክታጠፋቸውም ድረስ ውጋቸው’ ብሎ ልኮህ ነበር።
1 ሳሙኤል 15:19 (NASV)
ታዲያ እግዚአብሔር ን ለምን አልታዘዝህም? ለምርኮውስ ተስገብግበህ በ እግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ለምን አደረግህ?”
1 ሳሙኤል 15:20 (NASV)
ሳኦልም ሳሙኤልን መልሶ እንዲህ አለው፤ “ እግዚአብሔር ን ታዝዣለሁ፤ እግዚአብሔር በላከኝ መሠረት ሄጃለሁ፤ አማሌቃውያንን በሙሉ አጥፍቼ ንጉሣቸውን አጋግን አምጥቻለሁ።
1 ሳሙኤል 15:21 (NASV)
ሰራዊቱ ግን ከምርኮው ከተለዩት መካከል፣ ምርጥ ምርጡን በግና በሬ፣ በጌልገላ ለአምላክህ ለ እግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ ወስደዋል።”
1 ሳሙኤል 15:22 (NASV)
ሳሙኤልም እንዲህ አለ፤ “ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ደስ የሚለውን ያህል፣ እግዚአብሔር ፣ በሚቃጠል ቍርባንና መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ! መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም ከአውራ በግ ሥብ ይበልጣል።
1 ሳሙኤል 15:23 (NASV)
ዐመፅ እንደ ጥንቈላ ያለ ኀጢአት፣ እልኸኝነትም እንደ ጣዖት አምልኮ ያለ ክፉ ነገር ነው። አንተ የ እግዚአብሔር ን ቃል ስለ ናቅህ፣ እርሱም ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል።”
1 ሳሙኤል 15:24 (NASV)
ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ኀጢአት ሠርቻለሁ፤ የ እግዚአብሔር ን ትእዛዝና የአንተን መመሪያ ጥሻለሁ፤ ሕዝቡን ፈርቼ ስለ ነበር፣ የጠየቁኝን ታዝዣለሁ።
1 ሳሙኤል 15:25 (NASV)
አሁንም ኀጢአቴን ይቅር እንድትለኝ፣ ለ እግዚአብሔር ም እሰግድ ዘንድ ዐብረኸኝ እንድትመለስ እለምንሃለሁ።”