ዘካርያስ 13:7-9
ዘካርያስ 13:7-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ። በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል። ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ዘካርያስ 13:7-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣ በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ! እረኛውን ምታ፣ በጎቹም ይበተናሉ፤ እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የምድር ሁሉ፣ ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤ አንድ ሦስተኛው ግን በውስጡ ይቀራል፤ ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”
ዘካርያስ 13:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፥ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ። በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ክፍል ተቈርጠው ይሞታሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ሦስተኛውም ክፍል በእርስዋ ውስጥ ይቀራል። ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፥ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ዘካርያስ 13:7-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፍ ሆይ! ተባባሪዬ በሆነው በእረኛዬ ላይ ንቃ! በጎቹ ይበተኑ ዘንድ እረኛውን ምታ! እኔም በታናናሾቹ ላይ እጄን አነሣለሁ። በአገሪቱ ላይ ካሉት ሕዝቦች ከሦስቱ ሁለቱ እጅ ተመተው ይሞታሉ፤ ሆኖም ከሦስቱ አንዱ እጅ ይቀራል። እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
ዘካርያስ 13:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ። በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ሦስተኛው ተቈርጠው ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ፤ አንድ ሦስተኛው ክፍልም በእርሷ ይቀራል። አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።