ማሕልየ መሓልይ 8:1-14

ማሕልየ መሓልይ 8:1-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ የእ​ና​ቴን ጡት ትጠባ ዘንድ ማን በሰ​ጠህ? በሜዳ ባገ​ኘ​ሁህ ጊዜ በሳ​ም​ሁህ፥ ማንም ባል​ና​ቀ​ኝም ነበር። ይዤ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ ባገ​ባ​ሁህ፥ እኔ ከመ​ል​ካሙ የወ​ይን ጠጄ ከሮ​ማ​ኔም ውኃ ባጠ​ጣ​ሁህ ነበር። ቀኙ ባቀ​ፈ​ችኝ ግራ​ውም ከራሴ በታች በሆ​ነች ነበር። እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ወድዶ እስ​ኪ​ነሣ ድረስ ፍቅ​ሬን እን​ዳ​ት​ቀ​ሰ​ቅ​ሱ​ትና እን​ዳ​ታ​ስ​ነ​ሡት በም​ድረ በዳው ኀይ​ልና ጽን​ዐት አም​ላ​ች​ኋ​ለሁ። በልጅ ወን​ድ​ምዋ ላይ ተደ​ግፋ እንደ ማለዳ ደም​ቃና አብ​ርታ የም​ት​ወጣ ይህች ማን ናት? ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ከእ​ን​ኮይ በታች አስ​ነ​ሣ​ሁህ፤ በዚያ እና​ትህ አማ​ጠ​ችህ፥ በዚ​ያም ወላጅ እና​ትህ ወለ​ደ​ችህ። እንደ ቀለ​በት በል​ብህ፥ እንደ ቀለ​በ​ትም ማኅ​ተም በክ​ን​ድህ አኑ​ረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበ​ረ​ታች ናትና፥ ቅን​ዐ​ትም እንደ ሲኦል የጨ​ከ​ነች ናትና። ላን​ቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበ​ል​ባል ነው። ብዙ ውኃ ፍቅ​ርን ያጠ​ፋት ዘንድ አይ​ች​ልም፥ ፈሳ​ሾ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​አ​ትም፤ ሰው የቤ​ቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ አይ​ን​ቁ​ትም። እኅ​ታ​ችን ትንሽ ናት፥ ጡትም የላ​ትም፤ ስለ እር​ስዋ በሚ​ና​ገ​ሩ​ባት ቀን ለእ​ኅ​ታ​ችን ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት? እር​ስዋ ቅጥር ብት​ሆን የብር ግንብ በላ​ይዋ እን​ሥራ፤ ደጅ​አ​ፍም ብት​ሆን የዝ​ግባ ሳንቃ እን​ሥ​ራ​ላት። እኔ ቅጥር ነኝ፥ ጡቶ​ችም እንደ ግንብ ናቸው፤ በዚያ ጊዜ በፊቱ ሰላ​ምን እን​ደ​ም​ታ​ገኝ ሆንሁ። ለሰ​ሎ​ሞን በብ​ኤ​ላ​ሞን የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው፤ የወ​ይ​ኑን ቦታ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ አከ​ራ​የው፤ ሰው ሁሉ በየ​ጊ​ዜው ለፍ​ሬው አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር ያመ​ጣል። ለእኔ ያለኝ የወ​ይን ቦታ በፊቴ ነው፤ አንዱ ሺህ ለሰ​ሎ​ሞን፥ ሁለቱ መቶ ፍሬ​ውን ለሚ​ጠ​ብቁ ነው። በአ​ት​ክ​ልቱ ቦታ ሲኖር ሌሎች አዩት፥ ቃል​ህን አሰ​ማኝ። ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ፍጠን፤ በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋን ወይም የዋ​ሊ​ያን እን​ቦሳ ምሰል።

ማሕልየ መሓልይ 8:1-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ፣ እንደ ወንድሜ በሆንህ! ከዚያም ውጭ ባገኝህ፣ እስምህ ነበር፤ ታዲያ ማንም ባልናቀኝ! እኔም ወደ አስተማረችኝ፣ ወደ እናቴም ቤት፣ እጅህን ይዤ በወሰድሁህ ነበር፤ የምትጠጣውን ጣፋጭ የወይን ጠጅ፣ የሮማኔን ጭማቂም በሰጠሁህ። ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ ቀኝ እጁም ዐቅፎኛል። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት አማፅናችኋለሁ። ውዷን ተደግፋ፣ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተን ወለደችህ። በልብህ እንዳለ፣ በክንድህም እንደምትይዘው ማኅተም አስቀምጠኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች፣ ቅናቷም እንደ መቃብር ጨካኝ ናትና፤ እንደሚንቦገቦግ እሳት፣ እንደ ኀይለኛም ነበልባል ትነድዳለች። የውሃ ብዛት ፍቅርን ሊያጠፋ አይችልም፤ ፈሳሾችም አያሰጥሟትም፤ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይናቃል። ትንሽ እኅት አለችን፤ ጡትም ገና አላወጣችም፤ ስለ እርሷ በምንጠየቅበት ቀን ምን ማድረግ እንችል ይሆን? እርሷ ቅጥር ብትሆን፣ በላይዋ የብር መጠበቂያ ማማ እንሠራባታለን፤ በር ብትሆን፣ በዝግባ ዕንጨት እንከልላታለን። እነሆ እኔ ቅጥር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ማማ ግንቦች ናቸው፤ እኔም በዐይኖቹ ፊት፣ ሰላምን እንደሚያመጣ ሰው ሆንሁ። ሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑን ተክል ቦታም ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም የፍሬውን ዋጋ፣ አንድ አንድ ሺሕ ሰቅል ብር ያመጡለት ነበር። የወይኔ ተክል ቦታ የራሴ፣ የግሌ ነው፤ ሰሎሞን ሆይ፤ አንድ ሺሑ ሰቅል ለአንተ፤ ፍሬውን ለሚጠብቁ ደግም ሁለት መቶ ይሁን። አንቺ በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፤ ባልንጀሮቼ ድምፅሽን ይሰማሉ፤ እስኪ እኔም ልስማው። ውዴ ሆይ፤ ቶሎ ናልኝ፤ ሚዳቋን፣ ወይም በቅመም ተራራ ላይ የሚዘልል፣ የዋሊያን ግልገል ምሰል።

ማሕልየ መሓልይ 8:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ ምነው በሆንህ! በሜዳ ባገኘሁህ ጊዜ በሳምሁህ፥ ማንም ባልናቀኝም ነበር። መርቼ ወደ እናቴ ቤት ባገባሁህ፥ በዚያም አንተ ባስተማርከኝ፥ እኔም ከመልካሙ ወይን ጠጅ ከሮማኔም ውኃ ባጠጣሁህ ነበር። ግራው ከራሴ በታች በሆነች ቀኙም ባቀፈችኝ ነበር። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት እንዳታነሣሡትም አምላችኋለሁ። በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ። እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው። ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥ ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም፥ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል። እኛ ጡት የሌላት ታናሽ እኅት አለችን፥ ስለ እርስዋ በሚናገሩበት ቀን ለእኅታችን ምን እናድርግላት? እርስዋ ቅጥር ብትሆን የብር ግንብ በላይዋ እንሠራለን፥ ደጅም ብትሆን በዝግባ ሳንቃ እንከብባታለን። እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ። ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር። ለእኔ ያለኝ የወይን ቦታ በፊቴ ነው፥ ሰሎሞን ሆይ፥ ሺሁ ለአንተ፥ ሁለት መቶውም ፍሬውን ለሚጠብቁ ይሆናል። በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ቃል ያደምጣሉ፥ ቃልሽን አሰሚኝ። ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ምሰል።

ማሕልየ መሓልይ 8:1-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ በሆንክልኝ፤ በመንገድ ላይ አግኝቼ ብስምህ ማንም ሰው አይንቀኝም ነበር፤ ወደ ወላጅ እናቴ ቤት ባስገባሁህ ነበር፤ በዚያም ስለ ፍቅር ባስተማርከኝ ነበር፤ በሮማን ፍሬዬ ጭማቂ የጣፈጠውን መልካሙን የወይን ጠጅ ባጠጣሁህ ነበር። ግራ እጁን ያንተርሰኛል፤ በቀኝ እጁ ያቅፈኛል። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅ ሆይ! ፍቅር ራሱ ወዶ እስኪነሣ ድረስ ቀስቅሳችሁ እንዳታስነሡት ዐደራ እላችኋለሁ። በወዳጅዋ ትከሻ ላይ ደገፍ ብላ ከበረሓ የምትመጣ ይህች ማን ናት? ዱሮ እናትህ አንተን አምጣ በወለደችበት በፖም ዛፍ ሥር ቀስቅሼ አስነሣሁህ። በዘለዓለማዊ ፍቅር በልብህ ውስጥ እንደ ማኅተም አትመኝ፤ በክንድህም እንደ ማኅተም እኔን ብቻ ያዘኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት፤ ቅናትም እንደ መቃብር የከፋች ናት፤ የእሳትዋ ወላፈን እንደ እግዚአብሔር ወላፈን ነው። የውሃ ብዛት የፍቅርን እሳት ሊያጠፋ አይችልም፤ ጐርፍም ጠራርጎ ሊወስዳት አይችልም፤ ሰው ባለው ሀብት ሁሉ ፍቅርን ለመግዛት ቢሞክር ፍቅር በገንዘብ ስለማትገኝ ሰዎች ይዘባበቱበታል። ገና ጡት ያላወጣች ትንሽ እኅት አለችን፤ ለጋብቻ ብትጠየቅ ለዚህች ለእኅታችን የምናደርግላት ምንድን ነው? እርስዋ ቅጽር ብትሆን ኖሮ የብር ማማ እንሠራላት ነበር፤ እርስዋ የቅጽር በር ብትሆን ኖሮ ከሊባኖስ ዛፍ ሳንቃ የታነጸ መዝጊያ እንሠራላት ነበር። እነሆ፥ እኔ ቅጽር ነኝ፤ ጡቶቼም እንደ ቅጽር ማማዎች ናቸው፤ ከውዴ ጋር ስሆን እርሱ ደስታንና ሰላምን ያገኛል። ሰሎሞን በባዓልሃሞን የወይን ተክል ቦታ ነበረው፤ የወይኑንም ተክል ቦታ ለአትክልተኞች አከራየው፤ እያንዳንዳቸውም አንድ ሺህ ብር ያመጡለት ነበር፤ እኔ የግሌ የሆነ የወይን ተክል ቦታ አለኝ፤ ሰሎሞን ሆይ! አንተ አንድ ሺህ ብር፥ አትክልተኞቹ ሁለት መቶ ብር ልትወስዱ ትችላላችሁ። አንቺ የእኔ ሙሽራ ሆይ! በአትክልት ቦታ ሆነሽ ጓደኞቼ ድምፅሽን ለመስማት ይፈልጋሉ፤ እስቲ ለእኔ ድምፅሽን አሰሚኝ። ውዴ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ የቅመም ተክሎች በሚበቅሉባቸው ተራራዎች ላይ የሚዘል አጋዘን ወይም የዋልያ ግልገል ምሰል።

ማሕልየ መሓልይ 8:1-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ እንደ ወንድሜ ምነው በሆንህ! በሜዳ ባገኘሁህ ጊዜ በሳምሁህ፥ ማንም ባልናቀኝም ነበር። መርቼ ወደ እናቴ ቤት ባገባሁህ፥ በዚያም አንተ ባስተማርከኝ፥ እኔም ከመልካሙ ወይን ጠጅ ከሮማኔም ውኃ ባጠጣሁህ ነበር። ግራው ከራሴ በታች በሆነች ቀኙም ባቀፈችኝ ነበር። እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እርሱ እስኪፈልግ ድረስ ፍቅርን እንዳታስነሡት እንዳታነሣሡትም አስምላችኋለሁ። በውድዋ ላይ ተደግፋ ከምድረበዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት? ከእንኮይ በታች አስነሣሁህ፥ በዚያ እናትህ ወለደችህ፥ በዚያም ወላጅ እናትህ አማጠችህ። እንደ ማኅተም በልብህ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ አኑረኝ፥ ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናትና፥ ቅንዓትም እንደ ሲኦል የጨከነች ናትና። ፍንጣሪዋ እንደ እሳት ፍንጣሪ፥ እንደ እግዚአብሔር ነበልባል ነው። ብዙ ውኃ ፍቅርን ያጠፋት ዘንድ አይችልም፥ ፈሳሾችም አያሰጥሙአትም፥ ሰው የቤቱን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ቢሰጥ ፈጽሞ ይንቁታል። እኛ ጡት የሌላት ታናሽ እኅት አለችን፥ ስለ እርሷ በሚናገሩበት ቀን ለእኅታችን ምን እናድርግላት? እርሷ ቅጥር ብትሆን የብር ግንብ በላይዋ እንሠራለን፥ ደጅም ብትሆን በዝግባ ሳንቃ እንከብባታለን። እኔ ቅጥር ነኝ ጡቶቼም እንደ ግንብ ናቸው፥ በዚያን ጊዜ በፊቱ ሰላምን እንደምታገኝ ሆንሁ። ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር። ለእኔ ያለኝ የወይን ቦታ በፊቴ ነው፥ ሰሎሞን ሆይ፥ ሺሁ ለአንተ፥ ሁለት መቶውም ፍሬውን ለሚጠብቁ ይሆናል። በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ድምፅ ይሰማሉ፥ ድምፅሽን አሰሚኝ። ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ምሰል።