ማሕልየ መሓልይ 2:17 - Compare All Versions

ማሕልየ መሓልይ 2:17 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ልጅ ወን​ድሜ ሆይ፥ ቀኑ እስ​ኪ​ነ​ፍስ፥ ጥላ​ውም እስ​ኪ​ሸሽ ድረስ ተመ​ለስ፤ በቅ​መም ተራራ ላይ ሚዳ​ቋ​ውን ወይም የዋ​ላ​ውን እን​ቦሳ ምሰል።

ማሕልየ መሓልይ 2:17 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጎሕ ከመቅደዱ በፊት፣ ጥላውም ሳይሸሽ፣ ውዴ ሆይ፤ ተመለስ፤ ሚዳቋን ምሰል፤ ወይም በወጣ ገባ ኰረብቶች እንዳለው የዋሊያ ግልገል ሁን።

ማሕልየ መሓልይ 2:17 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ውዴ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እምቦሳ ምሰል።

ማሕልየ መሓልይ 2:17 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የሌሊቱ ጨለማ እስከሚወገድ፤ የማለዳው ነፋስ እስከሚነፍስ፤ ውዴ ሆይ! እንደ ዋልያ ወይም እንደ አጋዘን ግልገል በገደላማ ተራራዎች ላይ እየሮጥክ ተመለስ።

ማሕልየ መሓልይ 2:17 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ውዴ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፥ በወጣ ገባ ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እምቦሳ ምሰል።