ማሕልየ መሓልይ 2:14 - Compare All Versions

ማሕልየ መሓልይ 2:14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።

ማሕልየ መሓልይ 2:14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አንቺ በገደል ዐለት ንቃቃት፣ በተራሮችም ባሉ መደበቂያ ስፍራዎች ውስጥ ያለሽ ርግቤ ሆይ! ፊትሽን አሳዪኝ፤ ድምፅሽንም አሰሚኝ፤ ድምፅሽ ጣፋጭ፣ መልክሽም ውብ ነውና።

ማሕልየ መሓልይ 2:14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።

ማሕልየ መሓልይ 2:14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤ እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ ድምፅሽ አስደሳች ነው፤ ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።

ማሕልየ መሓልይ 2:14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ድምፅሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።