ሮሜ 8:9-14

ሮሜ 8:9-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እና​ንተ ግን ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ሕግ እንጂ ለሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ የም​ት​ሠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእ​ና​ንተ አድሮ ይኖ​ራ​ልና፤ የክ​ር​ስ​ቶስ መን​ፈስ ያላ​ደ​ረ​በት ግን እርሱ የእ​ርሱ ወገን አይ​ደ​ለም። ክር​ስ​ቶስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ከኀ​ጢ​አት ሥራ ለዩ፤ መን​ፈ​ሳ​ች​ሁ​ንም ለጽ​ድቅ ሥራ ሕያው አድ​ርጉ። ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ካደ​ረ​ባ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ከሙ​ታን ለይቶ ያስ​ነ​ሣው እርሱ አድ​ሮ​ባ​ችሁ ባለ መን​ፈሱ ለሟች ሰው​ነ​ታ​ችሁ ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ታል። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ አሁ​ንም በሥ​ጋ​ችን ሳለን በሥጋ ፈቃድ እን​ኖር ዘንድ አይ​ገ​ባም። እንደ ሥጋ ፈቃድ ብት​ኖሩ ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን በመ​ን​ፈ​ሳዊ ሥራ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ ብት​ገ​ድሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ የሚ​ሠሩ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ናቸው።