ሮሜ 7:5-6
ሮሜ 7:5-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
የሰውን ሕግ በሠራን ጊዜ ግን በኦሪት ሕግ ደካማነት ቅጣቱ ጸናብን፤ ሞትንም አፈራን። አሁን ግን ታስረንበት ከነበረው ከኦሪት ሕግ ነፃ ወጥተናል፤ ስለዚህ በብሉይ መጽሐፍ ሳይሆን በአዲሱ መንፈሳዊ ሕይወት እንገዛለን።
ያጋሩ
ሮሜ 7 ያንብቡሮሜ 7:5-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኀጢአተኛ በሆነ ተፈጥሮ ቍጥጥር ሥር ሳለን፣ ለሞት ፍሬ እንድናፈራ በሕግ የተቀሰቀሰው የኀጢአት መሻት በሥጋችን ላይ ይሠራ ነበር። አሁን ግን ቀድሞ ጠፍሮ አስሮን ለነበረው ሞተን፣ ከሕግ ነጻ ወጥተናል፤ ይህም አሮጌ በሆነው በተጻፈው ሕግ ሳይሆን፣ አዲስ በሆነው በመንፈስ መንገድ እንድናገለግል ነው።
ያጋሩ
ሮሜ 7 ያንብቡሮሜ 7:5-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤ አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።
ያጋሩ
ሮሜ 7 ያንብቡ