ሮሜ 7:4-5
ሮሜ 7:4-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወንድሞች ሆይ! እናንተ እንዲሁ የክርስቶስ አካል ስለ ሆናችሁ ከኦሪት ተለይታችኋል፤ ለእግዚአብሔርም ፍሬ እንድታፈሩ ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው ለዳግማዊ አዳም ሆናችኋል። የሰውን ሕግ በሠራን ጊዜ ግን በኦሪት ሕግ ደካማነት ቅጣቱ ጸናብን፤ ሞትንም አፈራን።
ያጋሩ
ሮሜ 7 ያንብቡሮሜ 7:4-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተም በክርስቶስ ኢየሱስ ሥጋ ለሕግ ሞታችኋል፤ ይህም ከሙታን ለተነሣው ለርሱ፣ ለሌላው ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው። ኀጢአተኛ በሆነ ተፈጥሮ ቍጥጥር ሥር ሳለን፣ ለሞት ፍሬ እንድናፈራ በሕግ የተቀሰቀሰው የኀጢአት መሻት በሥጋችን ላይ ይሠራ ነበር።
ያጋሩ
ሮሜ 7 ያንብቡሮሜ 7:4-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ። በሥጋ ሳለን በሕግ የሚሆን የኃጢአት መሻት ለሞት ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና፤
ያጋሩ
ሮሜ 7 ያንብቡ