ሮሜ 7:1-4 - Compare All Versions

ሮሜ 7:1-4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን! ሕግን ለሚ​ያ​ስ​ተ​ውሉ እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፤ ሰው በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ሁሉ ሕግ እን​ዲ​ገ​ዛው አታ​ው​ቁ​ምን? ባል ያላት ሴት ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ከእ​ርሱ ጋር በሕግ የታ​ሰ​ረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን በሚ​ስ​ት​ነት ታስ​ራ​በት ከኖ​ረ​ችው ሕግ የተ​ፈ​ታች ናት። ስለ​ዚህ ባልዋ በሕ​ይ​ወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብት​ሆን አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕግ ነፃ ወጥ​ታ​ለች፤ ለሌላ ወንድ ብት​ሆ​ንም አመ​ን​ዝራ አት​ባ​ልም። ወን​ድ​ሞች ሆይ! እና​ንተ እን​ዲሁ የክ​ር​ስ​ቶስ አካል ስለ ሆና​ችሁ ከኦ​ሪት ተለ​ይ​ታ​ች​ኋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍሬ እን​ድ​ታ​ፈሩ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ለተ​ነ​ሣው ለዳ​ግ​ማዊ አዳም ሆና​ች​ኋል።

ሮሜ 7:1-4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ወንድሞች ሆይ፤ ሕግን ለሚያውቁ ሰዎች እናገራለሁ፤ ሕግ በአንድ ሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው፣ ሰውየው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ መሆኑን አታውቁምን? አንዲት ያገባች ሴት ከባሏ ጋራ በሕግ የታሰረች የምትሆነው እርሱ በሕይወት እስካለ ድረስ ነው፤ ባሏ ቢሞት ግን ከጋብቻ ሕግ ነጻ ትሆናለች። ነገር ግን ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ሰው ብታገባ አመንዝራ ትባላለች፤ ባሏ ቢሞት ግን ሌላ ሰው ብታገባም እንኳ፣ ከዚያ ሕግ ነጻ ትሆናለች፤ አመንዝራ አትባልም። ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፤ እናንተም በክርስቶስ ኢየሱስ ሥጋ ለሕግ ሞታችኋል፤ ይህም ከሙታን ለተነሣው ለርሱ፣ ለሌላው ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው።

ያጋሩ
ሮሜ 7 NASV

ሮሜ 7:1-4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ወንድሞች ሆይ፥ ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና ሰው ባለበት ዘመን ሁሉ ሕግ እንዲገዛው አታውቁምን? ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት ሲኖር ከእርሱ ጋር በሕግ ታስራለችና፤ ባልዋ ቢሞት ግን ስለ ባል ከሆነው ሕግ ተፈትታለች። ስለዚህ ባልዋ በሕይወት ሳለ ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ ትባላለች፤ ባልዋ ቢሞት ግን ከሕጉ አርነት ወጥታለችና ለሌላ ወንድ ብትሆን አመንዝራ አይደለችም። እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ።

ሮሜ 7:1-4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አታውቁምን? የምናገረው ሕግን ለሚያውቁ ሰዎች ነው፤ ሕግ በሰው ላይ ሥልጣን የሚኖረው ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ ነው። ለምሳሌ፥ ያገባች ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከእርሱ ጋር በሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ከሞተ ግን ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ናት። ስለዚህ ባልዋ በሕይወት እያለ ሌላ ወንድ ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባልዋ ከሞተ ግን ከእርሱ ጋር ከታሰረችበት ሕግ ነጻ ትወጣለች፤ ሌላ ወንድ ብታገባም አመንዝራ አይደለችም። ወንድሞቼ ሆይ፥ የእናንተም ሁኔታ እንደዚሁ ነው፤ እናንተ የክርስቶስ አካል ክፍል ስለ ሆናችሁ በሞት የመለየትን ያኽል ከሕግ ተለይታችኋል፤ ስለዚህ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ፍሬ እንድናፈራ ከሞት የተነሣው የክርስቶስ ወገኖች ሆናችኋል።

ሮሜ 7:1-4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ወንድሞች ሆይ! ሕግን ለሚያውቁ እናገራለሁና፤ ሕግ ሰውን የሚገዛው በሕይወት እስካለ ድረስ ብቻ መሆኑን አታውቁምን? ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ በሕግ ታስራለችና፤ ባሏ ቢሞት ግን ከባል ሕግ ተፈትታለች። ስለዚህ ባሏ በሕይወት እያለ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነፃ ናት፥ ሌላ ባል ብታገባ አመንዝራ አይደለችም። ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ! እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ እንድትሆኑና ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ ነው።