ሮሜ 6:1-4
ሮሜ 6:1-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እንግዲህ ምን እንላለን? የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲበዛ ኀጢአት እንሥራን? አይደለም። ከኀጢአታችን የተለየን እኛ እንግዲህ እንዴት ዳግመኛ በእርስዋ ጸንተን መኖር እንችላለን? ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቅን እኛ ሁላችን በሞቱ እንደ ተጠመቅን ሁላችሁ ይህን ዕወቁ። በሞቱም እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን፤ እርሱ ክርስቶስ በአባቱ ጌትነት ከሙታን እንደ ተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐዲስ ሕይወት እንኖራለን።
ሮሜ 6:1-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ ኀጢአት እየሠራን እንኑር? ከቶ አይሆንም፤ ለኀጢአት ሞተናል፤ ታዲያ እንዴት አድርገን ከእንግዲህ በርሱ እንኖራለን? ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋራ አንድ እንድንሆን የተጠመቅን ሁላችን፣ ከሞቱ ጋራ አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ፣ እኛም እንዲሁ በአዲስ ሕይወት እንድንኖር በጥምቀት ሞተን ከርሱ ጋራ ተቀብረናል።
ሮሜ 6:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም። ለኃጢአት የሞትን እኛ ወደ ፊት እንዴት አድርገን በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
ሮሜ 6:1-4 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እንግዲህ ምን እንላለን? የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ጸንተን እንኑርን? አይደለም! እኛ በሞት የመለየትን ያኽል ከኃጢአት የተለየን ሆነን ሳለ እንዴት በኃጢአት ጸንተን እንኖራለን? ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቅን ሁሉ የሞቱም ተካፋዮች ለመሆን መጠመቃችንን አታውቁምን? በጥምቀት ከእርሱ ጋር በተቀበርን ጊዜ የእርሱም ሞት ተካፋዮች ሆነናል፤ ስለዚህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሞት እንደ ተነሣ እኛም በአዲስ ሕይወት እንኖራለን።
ሮሜ 6:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ ኃጢአት በመሥራት እንቀጥል? በጭራሽ! ለኃጢአት የሞትን እስካሁን እንዴት በእርሱ እንኖራለን? ወይስ ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ ለመሆን የተጠመቅን ሁላችን ከሞቱ ጋር አንድ ለመሆን እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? ስለዚህ በአብ ክብር ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንኖር፥ በጥምቀት አማካኝነት በሞት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል።