ሮሜ 5:3-4 - Compare All Versions

ሮሜ 5:3-4 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የም​ን​መካ በእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ከ​ራ​ችን ደግሞ እን​መ​ካ​ለን እንጂ፤ መከራ በእና ላይ ትዕ​ግ​ሥ​ትን እን​ደ​ሚ​ያ​መጣ እና​ው​ቃ​ለ​ንና። ትዕ​ግ​ሥ​ትም መከራ ነው፤ በመ​ከ​ራም ተስፋ ይገ​ናል።

ሮሜ 5:3-4 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤

ያጋሩ
ሮሜ 5 NASV

ሮሜ 5:3-4 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤

ሮሜ 5:3-4 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚህ ብቻ ሳይሆን መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝልን ስለምናውቅ በመከራችንም እንመካለን። ከትዕግሥትም በፈተና መጽናት፥ ከመጽናትም ተስፋ ይገኛል።

ሮሜ 5:3-4 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በዚህ ብቻ ሳይሆን፥ መከራ ጽናትን እንደሚያስገኝ ስለምናውቅ በመከራም ጭምር እንመካለን፤ ጽናትም የተፈተነ ባሕርይን ያስገኝልናል፥ የተፈተነ ባሕርይም ተስፋን፤